Tender Detail

Tender Details

  • Deadline18 Aug 2022, 10:09 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ አኩሪ አተር ፣ ቦለቄ ፣ ሩዝ እና ለምግብነት የሚዉሉ ሰብሎች ፣ ብጣሪዎች እና ያገለገሉ ጆንያዎችን ለመሸጥ እና የተለያዩ የኬሚካልና የመርጫ መሳሪያ ለመግዛት ይፈልጋል



ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ በሀገር ውስጥ ገበያ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ እና

  • የተለያዩ ለዘር የሚዉል ንፁህ ምርጥ ዘር ከዘር የተረፈ በባለሙያ የተረጋገጠ አኩሪ አተር ፣ ቦለቄ ፣ ሩዝ እና ለምግብነት የሚዉሉ ሰብሎች ፣ ብጣሪዎች እና ያገለገሉ ጆንያዎችን ለመሸጥ እና
  • የተለያዩ የኬሚካልና የመርጫ መሳሪያ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡-

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ፤ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፤ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት /ቲን/ ፎቶ ኮፒ በማድረግ የማይመለስ ብር 50 በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር/10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ባሕር ዳር አለ በጅምላ (ጅንአድ) ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢንተርኘራይዙ መስሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ መግዛት ይችላሉ
  2. ተጫራቾች ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች የአሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከኢንተርፕራይዙ ጋር ዝርዝር ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው መሠረት የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ በማለት የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር/10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በሥራ ሰዓት በኢንተርኘራይዙ ዋና መስሪያ ቤት /ባሕር ዳር/ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በአስረኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ይዘጋል፡፡ በዚሁ ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሸጋገራል፡
  6. ድርጅቶች ዋጋ ከሞሉበት ሰንጠረዥ ላይ እርጥብ ማህተም ወይም ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
  7. የኬሚካልና ፀረ ተባይ ግዥዎችን በሚመለከት በግብርና ሚኒስቴር መመዝገቡን የሚገልጽ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ያገለገሉ ጆንያዎችና ብጣሪን በተመለከተ ንግድ ፈቃድ እንዲያቀርብ አይገደድም፡፡
  9. ግዠዉን በተመለከተ ባህር ዳር ዋናዉ መስሪያ ቤት መጋዘን መድሀኒዓለም አካባቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡ ሌሎች ሰብሎችን በተመለከተ ባህር ዳር ፣ ኮምቦልቻ ፣ እንጅባራ ፣ ብር ሸለቆ እና ደብረ ብርሀን የሚገኙ ሲሆን ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ይመልከቱ
  10. ኢንተርኘራይዙ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ኢንተርኘራይዙ ለግዥም ሆነ ለሽያጭ ከተጠየቀዉ ዉስጥ እንደአስፈላጊነቱ መጠን አስከ 50 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኢንተርፕራይዙ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 0582266002 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0583208415/0918016935 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ

Save Tender