Tender Detail

Tender Details

  • Deadline24 Aug 2022, 10:08 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የኮምፒውተር ወረቀት ዕቃዎች እና የህንፃ ቀለም ቅብ ስራዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በ2015 በጀት ዓመት በዘርፉ አግባብነት ያለዉ የስራ ፈቃድ ያላቸዉ አቅራቢ ድርጅቶች ጥቅል ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊዉ ድርጅት ላይ

  • የኮምፒውተር ወረቀት ዕቃዎች እና
  • የህንፃ ቀለም ቅብ ስራዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዘርፉ አግባብነት ያለዉ እና በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው።
  2.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው።
  3. በዘርፉ አግባብነት ያለዉ የስራና የንግድ ፈቃድ ያለዉ።
  4. የግዥ መጠን ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምሰክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  6.  ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የመጫረቻ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 105 ድረስ በመምጣት ለእያንዳንዱ የመጫረቻ ሰነድ አይነት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
  7.  የሚገዙ የኮምፒተር ወረቀት ዕቃዎች እና የቀለም ቅብ ስራዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፒስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና /ቢን ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃዉን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ስፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋሰትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በኮርፖሬሽኑ የገቢ ደረሰኝ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋ።
  9. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸዉን የኮምፒውተር ወረቀት ዕቃዎች እና የህንፃ ቀለም ቅብ ስራዎች እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አቫሪ ሆኖ በቀረበዉ መሰረት ይሆናል።
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታዎች በማድረግ በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ በግዥ /ፋይ/ንብ /አስ/ ዳይሬክቶሬት አንደኛ ፎቅ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 103 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 2014 ዓ/ም በተከታታይ ቀናት 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል በቢሮ ቁጥር 103 በ16ኛው ከቀኑ 4፡00 ላይ ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻዉ ዕለት የህዝብ በዕል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለዉ ቀን 3፡00 ላይ ታሽጎ 3፡30 ላይ ይከፈታል።
  12. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ /አማራጭ/ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 103 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058-226- 50-02 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058-320-97-35 ማግኘት ይችላሉ።


የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

Save Tender