ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በ2014 ዓ.ም. በጀት ለሚያስገነባው የማስፋፊያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ዳሞት ሶሬ ፣ ቦሎሶ ቦምቤ ፣ ኦፋ ፣ ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳዎች ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ(አ.ማ.) ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በ2014 ዓ.ም. በጀት ለሚያስገነባው የማስፋፊያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ሎት-2 ዳሞት ሶሬ ፣ ቦሎሶ ቦምቤ ፣ ኦፋ ፣ ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳዎች ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ የሥራ ተቋራጮች፡-
- ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተመዘገቡ ደረጃቸው GC-4/BC-4 እና ከዛ በላይ የሆኑ ፣ ግብር በመክፈል በ2014 ዓ.ም. ፈቃዳቸውን ያሳደሱ የታደሰ ብቃት ማረጋጫ ምስክር ወረቀት ያላቸው ተ.እ.ታ(VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ ቲን(TIN) መለያ ቁጥር ያላቸው ፣ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ፣ ህጋዊ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ከሚመለከተው ክፍል የተሰጠ ታክስ ክሊራንስ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ከሚመለከተውአካል የተሰጠ ወቅታዊ ታክስ ክሊራንስ VALID TAX CLEARANCE ሰርተፍኬት ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በፌዴራል ግዥ እና የመንግስት ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዶክመንቱ የማይመለስ ብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር) በመክፈል ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ(አ.ማ.) ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር---የንግድ ፈቃዳቸውን ዋናውን (Original) በመያዝ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ባንክ ጋራንቲ 450,000.00(አራት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የግንባታ ሳይቶችን ጉብኝት ተደርጎ ከወረዳው ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ወይም ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ቢሮ የሳይት ጉብኝት ድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሠነድ ኦሪጅናሉን እና ቴክኒካል ሠነድ ኦሪጅናሉን አንድ ላይ በማሸግ እና 2 የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሁሉንም ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ሙሉ አድራሻቸውንና የኘሮጀክቱን ስም በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ30 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ሰዓት በኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ(አ.ማ.) ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 3-G+ 2 ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም።
- ተጫራቾች በጨረታ መክፈቻ ዋጋና በሂሳብ ማስተካከያ ዋጋ ልዩነት ከ2% በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም የሚያንስ መሆን የለበትም።
- ተጫራቾች በዞኑ ውስጥ ሲሰሩ ምንም ማስጠንቀቂያ ያልተሰጣቸው መሆን አለባቸው።
- በተጨማሪ እንደገና ተሻሽሎ የወጣው የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 28/2010 ፣ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የወጣ የኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ መመሪያ ቁጥር 648/2013 እና በዚሁ መመሪያ ላይ ማሻሻያ የያዘ ሰርኩላር ተግባራዊ ይሆናል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ. 046 552 4450 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።
ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ(አ.ማ.) ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
