ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በ2014 ዓ.ም. በጀት ለሚያስገነባው የአባላ አባያና የድምቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በ2014 ዓ.ም. በጀት ለሚያስገነባው የአባላ አባያና የድምቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ( ሎት-1 ድምቱ ፣ ሎት-2 አባላ አባያ) ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሱ የሥራ ተቋራጮች፡-
- በኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተመዘገቡ ደረጃቸው GC-4/BC-4 እና ከዛ በላይ የሆኑ ፣ ግብር በመክፈል በ2014 ዓ.ም. ፈቃዳቸውን ያሳደሱ ፣ የታደሰ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያላቸው ፣ ተ.ኦ.ታ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ቲን (TIN) መለያ ቁጥር ያላቸው ፣ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ፣ ህጋዊ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ፣ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ከሚመለከተው ክፍል የተሰጠ ታክስ ክሊራንስ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ወቅታዊ ታክስ ክሊራንስ (VALID TAX CLEARANCE) ሰርተፍኬት ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በፌዴራል ግዥ እና የመንግስት ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዶክመንቱ የማይመለስ ብር 500.00(አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ(አ.ማ.) ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ግ/ፋን/አስ/ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር --- የንግድ ፈቃዳቸውን ዋናውን(Original)በመያዝ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲ.ፒ.ኦ) ባንክ ጋራንቲ ለእያንዳንዱ ሎት 250,000.00(ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች አንድ ተጫራች ከአንድ ሎት በላይ መጫረት አይችልም።
- ተጫራቾች የግንባታ ሳይቶችን ጉብኝት ተደርጎ ከወረዳው ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ወይም ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ቢሮ የሳይት ጉብኝት ድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሠነድ ኦሪጅናሉን እና ቴክኒካል ሠነድ ኦሪጅናሉን አንድ ላይ በማሸግ እና 2 የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሁሉንም ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ሙሉ አድራሻቸውንና የፕሮጀክቱን ስም በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ30 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ሰዓት በኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ(አ.ማ.) ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር G+2-3 ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም።
- ተጫራቾች በጨረታ መክፈቻ ዋጋና በሂሳብ ማስተካከያ ዋጋ ልዩነት ከ2% በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም የሚያንስ መሆን የለበትም።
- ተጫራቾች በዞኑ ውስጥ ሲሰሩ ምንም ማስጠንቀቂያ ያልተሰጣቸው መሆን አለባቸው።
- በተጨማሪ እንደገና ተሻሽሎ የወጣው የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 28/2010 በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የወጣ የኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ መመሪያ ቁጥር 648/2013 እና በዚሁ መመሪያ ላይ ማሻሻያ የያዘ ሰርኩላር ተግባራዊ ይሆናል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ. 046 552 4450 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።
ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
