Tender Detail

Tender Details

  • Deadline24 Aug 2022, 9:49 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

የፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ለድርጅታችን አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽዳት እቃዎች ፣ የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የጥበቃ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል



የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያው ቁጥር 002/2015

የፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ለድርጅታችን አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት 1. የተለያዩ የጽዳት እቃዎች ፣ 
  • ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ 
  • ሎት 3. የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ፣ 
  • ሎት 4. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣ 
  • ሎት 5. የጥበቃ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1.ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ለእያንዳንዳቸዉ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 36 (ካሸር ቢሮ) በመምጣት መግዛት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ፣ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ኮፒ እና የአቅራቢዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid bond) የሚሸጡበትን ዋጋ ከሎት 1 እስከ ሎት 4 2% እንዲሁም ለሎት 5. 20,000 (ሃያ ሺህ ብር ) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች በሎት 1 ፣ 2 ፣ 3 ፣ 4 እና ሎት 5 ለተመለከተው በኤንቨሎፕ በማሸግ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ በሎጅስቲክስና ሰፕላይ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተቀመጠ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 15 ተከታታይ ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በሎጀስቲክስና ሰፕላይ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በበአል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታዉ በሚቀጥለዉ የመጀመሪያ የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይከፈታል።

6.ተጫራቾች በሎት 1 እና ሎት 2 ሳምፕል ማቅረብ ያለባቸዉ ሲሆን ለሎት 3 እና 4 የእቃዎችን ሳምፕል በፎቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7.ተጫራቾች በሎት 3 ሎት 4 እና ሎት 5 ለተመለከተዉ ቴክኒካል እና የፋይናንሽያል ፕሮፓዛል ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማዘጋጀትና በኤንቨሎፕ በማሸግ ጋዜጣዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ በሎጀስቲክስና ሰፕላይ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 በተቀመጠ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ።

8. ድርጅታችን ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

አድራሻ፡- የፐብሊክ ሰርቪስ የትራንስፖርት አገልግሎት

ከሜክሲኮ ወደ ልደታ ቤተክርስቲያን የሚወስደዉ መንገድ ላይ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0910 82 78 59

የፐብሲክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት

Save Tender