Tender Detail

Tender Details

  • Deadline06 Sep 2022, 6:28 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኢንስቲትዩት በተቋሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ የአስተዳደር ቢሮ ግንባታ ሥራ መስፈርቶችን የሚያሟላ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

በ/ደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ትምህርት ሥልጠና ቢሮ የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኢንስቲትዩት በተቋሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ የአስተዳደር ቢሮ ግንባታ ሥራ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟላ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት

  1. ደረጃቸው GC-5/ BC-5 እና ከዚህ በላይ የሆነ
  2. ፈቃዳቸውንና የምዝገባ ሰርተፍኬታቸውን ለ2014 ዓ.ም. ያሳደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
  3. ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ዶክመንት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ቀናት ከኮሌጁ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የሥ/ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች 500,000( አምስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም ባንክ ዋስትና ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰንድ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግና ጠቅላላውን ሠነድ በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 -6:00 ሰአት ኮሌጁ ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መክተት አለባቸው ።
  6. ጨረታው በ31ኛው ቀን ከቀኑ ከ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  7. 31ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  8. ኮሌጁ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ተጨማሪ መረጃ ከሰነዱ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እያሳወቅን የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት እንደገና ተሻሽሎ በወጣው የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 28/2010 እና በመመሪያው ላይ የተደረገውን ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ሰርኩላር ተፈፃሚ ያደርጋል።

ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ፦046 881 3659

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኢንስቲትዩት

አርባ ምንጭ

Save Tender