የቤትና መጋዘን የሐራጅ ሽያጭ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት አቶ ኤልያስ ዮናስ እና በፍ/ባለዕዳ ሀጅ በሽር መሀመድ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 86032 ቀን በ10/3/2014 ዓ.ም. በመ/ቁ 76360 በ3/12/2013 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 የቤ.ቁ 1042 የሆነው ቤትና መጋዘን ኮ/ቀ 06/19/1389/00 የቦታ ስፋት 568 ካ.ሜ. ያህል አዋሳኞች በሰሜን የቀበሌ፣ በደቡብ ከመንገድ በምስራቅ ቀበሌ በምዕራብ አስካለ ገ/ማርያም ሆኖ በአጠቃላይ ይዞታ ውስጥ ቦታው የስፍር መንገድ 41 ካ.ሜ. የሚነካ ሆኖ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 1,264,000 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ስልሳ አራት ሺህ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ግዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል። የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬከቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፤ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናት ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለበቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጎበኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት።
በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ ሐራጁ ጎድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬቱ የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን።
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች
የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
