Tender Detail

Tender Details

  • Deadline24 Aug 2022, 5:42 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

አደአ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ 2015 ዓ.ም. የጽሕፈት መሳሪያዎች ፣ ጥቃቅን ቋሚ የቢሮ እቃዎች እና የቀለም ሙሌት ፣ የፅዳት እቃዎች ፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣ የደንብ ልብስ እና የስፌት ዋጋ ፣ የግብርና መሳሪያዎች አካፋ ፣ ዶማ እና የደን ዘር ለቴክኒክና ሙያ አገልግሎት የሚውሉ መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ 01/2015

አደአ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ 2015 ዓ.ም. በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዢ አይነቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት1. የጽሕፈት መሳሪያዎች ፣ ጥቃቅን ቋሚ የቢሮ እቃዎች እና የቀለም ሙሌት
  • ሎት2. የፅዳት እቃዎች
  • ሎት3. ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  • ሎት4. የደንብ ልብስ እና የስፌት ዋጋ
  • ሎት5. የግብርና መሳሪያዎች አካፋ ፣ ዶማ እና የደን ዘር
  • ሎት6. ለቴክኒክና ሙያ አገልግሎት የሚውሉ መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
  1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የቲን ቁጥር፤ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ) ኢት.ንግድ ባክ አካውንት ቁጥር 1000011143656 ገቢ በማድረግ ከአደአ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 ሰነድ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛኑ ዕለት ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ በዓል ላይ ከዋለ በማግስቱ የሚከፈት ይሆናል።
  3. የሚገዙት ዕቃዎች ናሙና (Sample) በተጠየቁት መሠረት ተሟልቶ ካልቀረቡና ማንኛውም አይነት ስህተት ቢፈጸም ላፊነቱ የአቅራቢ ድርጅት ይሆናል።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃዎች አይነት ወይም ናሙና ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ዘወትር በስራ ሰዓት በመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 9 ናሙናቸውን የራሳቸው መለያ በማድረግ ማቅረብ የሚቻል ሲሆን አይነቶቹም የፎቶ ኮፒ ወረቀት፣ ስክሪብቶ፣ አጀንዳ፣ ፍላሽ፣ መዝገቦች፣ የእጅ ካርቦን፣ ማርከር፣ ኡሁ፣ ፍሉድ፣ የደንብ ልብስ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው ናሙና ተጠይቆበት ያልቀረበ ከሆነ ያልቀረበበት የጨረታ ሰነድ ቁጥር ውድቅ ይሆናል።
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ ብር 4000 (አራት ሸህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ማስያዝ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን እና አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው ማህተም በየገጹ በማድረግ በድርጅቱ ባለቤት ወይም በሥራ አስኪያጁ መፈረም አለበት።
  7. አሸናፊዎች ውል ለመፈጸም ለውል ማስከበሪያ ያሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ለውል ማስከበሪያ ዋስትና ሰነድ የተያዘ CPO ውል ከተፈጸመበት ዕለት ጀምሮ ለ28 ቀናት ይቆያል።
  8. የጨረታው ሰነድ የቴከኒካል እና ፋይናንሻል (Techinical and Financial) (የሎቱ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ መግባት አለበት ቴከኒካል ያላለፉት ተወዳዳሪዎች ወደ ፋይናንሻል ውድድር የማይገቡ ሲሆን ሌሎች መመሪያዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው መመሪያ መሰረት ይሆናል።
  9. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስ.ቁ 011 433 5405/011 433 5404 (ቢሾፍቱ)

በኦሮሚያ ክ/መ/ በምስራቅ ሸዋ ዞን አደአ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

 

Save Tender