የመንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ጎማዎች ፣ ዘይት እና ቅባት ፣ የመበየጃ ማሽን ለመግዛት ይፈልጋል
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የመንቆረር ኮንስትራከሽን ኢንተርፕራይዝ በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጀም ዞን በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን
- ሎት 1ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ ለማሸነሪና ተሽከርካሪ የተለያየ መጠን ያላቸውን ጎማዎች ብዛት–186 ፣
- ሎት2 ዘይት እና ቅባት ብዛት– 30 በርሜል
- ሎት 3 የመበየጃ ማሽን ብዛት =3 በዘርፉ ከተሰማሩት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡
- ተጫራቾ የምትጫረቱበትን ዋጋ በጥንቃቄ በመሙላት በሰም በታሸገ ፖስታ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ቀናት በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 7 ማስገባት አለባችሁ።
- ጨረታው የጨረታ ማስገቢያው በተጠናቀቀ በቀጣይ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ላይ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በበአላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።ሆኖም በራሳቸው ፈቃድ በመከፈቻው ቀን ባይገኙ የጨረታውን መከፈት አያስቀረውም።
- ተጫራቾች የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ በዘርፉ ህጋዊ የተመዘገበ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር የገበሩና የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- . ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር ሰነዱን መንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ በነፃ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንh ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው:
- አሸናፊው ድርጅት ሚያቀርባቸው እቃዎች በጨረታው ዝርዝር መሰረት በባለሙያ ተረጋግጦ ማለፍ አለባቸው።
- አሸናፊው የሚለየው በየምድባቸው በሎት ወይም በጥቅል ይሆናል።
- አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርበውን ቃዎች በራሱ ወጪ ኢንተርፕራይዙ ንብረት ክፍል ድረስ ገቢ ማድረግ አለባቸው:
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ 10% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባን ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለበት።
- ተጫራቾች አሸናፊመሆናቸው ከተገለፀላቸው ባሉት 7 /ሰባት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ውል በመያዝ የታዘዙ ቃዎችን ደ/ማርቆስ ከተማ መንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ኢንተርፕራይዙ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፈልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁፕር 0930 95 83 51 ደውለው መጠየቅ ይችላሱ።
በምስ/ጎጃም ዞን በደ/ማ ከተማ/ስ መንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት
