Tender Detail

Tender Details

  • Deadline06 Sep 2022, 5:11 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሄር ቤተክርስቲያን እርዳታና ልማት ማህበር ገብስ ፣ የሽሮ አተር (የተከካ) ፣ አጃ ፣ ጥሬ ቡና ፣ ድፍን ምስር ፣ ጤፍ ፣ ፉርኖ ዱቄት እና ዘይት (5ሊ) የዳቦ ምጣድ የኤሌክትሪክ እንጀራ ምጣድ ፣ እና ላቀች ምጣድ ለመግዛት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቀጥር ADA/328/22

የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሄር ቤተክርስቲያን እርዳታና ልማት ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ ማለትም በቂርቆስ፣ በቦሌ፣ በየካ፣ በንፋስ ስልክ፣ እና ኮልፌ ቀራንዮ ለሚገኙ ከ312 በላይ ሴት ተጠቃሚዎቹ አነስተኛ ንግድ ለማስጀመር ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የተለያዩ ምግብ ነክ እና ምግብ ለማዘጋጀት የሚያገለግሉ ዕቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል እነርሱም፡- ገብስ፣ የሽሮ አተር (የተከካ)፣ አጃ፣ ጥሬ ቡና፣ ድፍን ምስር፣ ጤፍ፣ ፉርኖ ዱቄት እና ዘይት (5ሊ) የዳቦ ምጣድ የኤሌክትሪክ እንጀራ ምጣድ፣ እና ላቀች ምጣድ፣

በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር በኢትዮ-ቻይና መንገድ ወንጌላዊት ህንጻ አጠገብ ሜሪስቶፕስ ክሊኒክ ከፍ ብሎ በሚገኘው ቢሯአችን ድረስ በአካል በመገኘት የጨረታን ሰነድ ከግዥ ክፍል መግዛት ይችላሉ። ጨረታው ከሰኞ ነሐሴ 02/2014 እስከ ነሐሴ 13/2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ለተጫራቾች ከፍት ይሆናል።

ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፦ 

  • የታደሰ የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር መያዝ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100 ብር (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የእርዳታና ልማት ማህበር ግዥ ከፍል ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በድርጅታችን ሥም “የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርሰቲያን የእርዳታና ልማት ማህበር” ከኢትየጵያ ንግድ ባንክ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) አሰርተው ከዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ ጋር በሰም በታሽገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ወይም ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • የተሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት CPO ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  • ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን እና ሌሎች ተፈላጊ መረጃዎችን በአንድ ፖስታ በማሸግ 1 ኦርጅናል እና 1 ኮፒ በመለያየት በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
  • በጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ከብ ማህተምና ፊርማ ማድረግ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ቢያጋጥም በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ነጠላ ዋጋ በማድረግ በጨረታ ሰነዱ በመሙላት በሰም በታሸı ኤንቨሎፕ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  • ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኞ ነሐሴ 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይሆናል።
  • አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች የሚያቀርበው በ10 ቀናት ውስጥ ማለትም ከነሐሴ 17 ቀን እስከ ነሐሴ 27/2014 ይሆናል።
  • አዲስ አበባ ወይም አዲስ አበባ አከባቢ ማከፋፈያ ወይም ሱቅ ያለው መሆን አለበት።
  • እቃውን ተጠቃሚዎቻችን ሱቃችሁ ድረስ መጥተው የሚወስዱ ይሆናል።
  • ልማት ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • የአከፋፈል ሁኔታ ክፍያው የሚፈፀመው ተጠቃሚዎቻችን በወሰዱት የእቃ እና ዋጋ መጠን ለአሸናፊው ድርጅት በሚያቀርቡት ኩፖን እና የአቅራቢውን ድርጅት ሰነድ እና ደረሰኝ በማመሳከር በዋናው ቢሮአችን ይሆናል።
  • ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0984 70 24 33 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሄር ቤተክርስቲያን እርዳታና ልማት ማህበር

Save Tender