Tender Detail

Tender Details

  • Deadline28 Aug 2022, 4:40 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

የኦሮሚያ የግብርና ሕብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ገላን ከተማ የሚገኘው መጋዘን ያለው በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ የጤፍ ፣ ሰሊጥ ፣ አኩሪ አተር እና ማሾ ምርት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ የግብርና ሕብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ገላን ከተማ የሚገኘው መጋዘን ያለው

  • በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ የጤፍ ፣ ሰሊጥ ፣ አኩሪ አተር እና ማሾ ምርት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ምርቱን መግዛት የሚፈልግ ተጫራች ግለሰብ ወይም ድርጅት ከዚህ ቀጥሎ ያሉ መስፈርቶችን በማሟላትና በአካል በመገኘት በተዘጋጀው ፎርም ላይ ዋጋ ሞልታችሁ በማስገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። መስፈርቶቹም የሚከተሉት ናቸው።

  1. ተጫራቹ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የዓመቱን ግብር የከፈሉ እና ቲን ሰርተፍኬት አያይዛችሁ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  2. ተጫራቹ ለጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ ዋጋውን 10% በሲፒኦ ቢድ ቦንድ አሰርተው ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቹ ለጨረታ ሰነድ ግዢ የማይመለስ ብር 200( ብር ሁለት መቶ) በፌዴሬሽኑ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነድ መግዛት አለባቸው።
  4. ማንኛውም ተጫራች በድርጅታችን ዋና ቢሮ አ/አበባ በአካል በመገኘት በተዘጋጀው ፎርም ላይ ዋጋ ሞልተውይህ ማስታወቅያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21(ሀያ አንድ) የስራ ቀናት ማስገባት አለባቸው።
  5. የጨረታ መክፈቻ ቀን በ22ኛው ቀን ከ8፡oo -9፡oo ሰዓት ነው።
  6. ከጨረታ መነሻ ዋጋ በታች ወይም እኩል ዋጋ የሰጠ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል።
  7. የጨረታ ሰነድ ላይ የተገለጸው የምርት መጠን ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
  8. ተጫራቾች አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
  9. አሸናፊው የገዛውን ንብረት ሙሉ ዋጋ በመክፈል በ10(አስር) ቀን ውስጥ ከፌዴሬሽኑ መጋዘን ማንሳት ይኖርባቸዋል።
  10. የጨረታው ውጤት ድርጅቱ አሸናፊውን በስልክ የሚያሳውቅ ወይም ውጤቱን የሚለጥፍ ይሆናል።

አድራሻ፡-ድርጅታችን ከኡራኤል ቤተ ክርስቲያን አለፍ ብለው የኦሮሚያ ፀረ- ሙስና ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 0929 90 46 91/0944 10 09 68 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የኦሮሚያ የግብርና ሕብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን

Save Tender