Tender Detail

Tender Details

  • Deadline02 Oct 2022, 4:35 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Construction Equipment And Machinery

የደቡብ ምዕራብ መንገዶች ባለስልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች ማለትም የገልባጭ መኪና እስከነ ሎደር እና የማሽነሪ መሳሪያዎች ዶዘር ፣ ግሬደር ፣ ኤክስካቫተር እና ሮለር ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ደ/ምኢመባ 0006/14

መ/ቤታችን የደቡብ ምዕራብ መንገዶች ባለስልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች ማለትም የገልባጭ መኪና እስከነ ሎደር እና የማሽነሪ መሳሪያዎች ዶዘር፣ ግሬደር፣ ኤክስካቫተር እና ሮለር ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

በመሆኑም፦

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት ና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በተለየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት የቢሮ ቁጥር 02 መውሰድ ይችላሉ።
  4. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነት ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።
  5. አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 25ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ድረስ ይሆናል። ጨረታው በዚያኑ ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጠዋት 2፡30 ይሆናል።
  6. ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልከ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
  7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም
  8. በ2014 በጀት ዓመት መ/ቤቱ ባወጣው ጨረታ አሸናፊ ሆነው በማንኛውም ምክንያት ወደ ስራ ያልገቡት ተጫራቾች መወዳደር አይችሉም።
  9. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

1. ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።

የደቡብ ምዕራብ መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት

ግብ/አቅ/አስ/ደጋፌ/የሥራ ሂደት ግዥና ንብ/አስ/ር

ቦንጋ ኢትዮጵያ

Save Tender