በሲዳማ ብ/ክ/መ የአ/ወ/ወ/ፋ/ል/ጽ/ቤት የተለያዩ ዓይነት መድኃኒቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብ/ክ/መ የአ/ወ/ወ/ፋ/ል/ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት ለአ/ወ/ወ/እን/ዓ/ሀ/ል/ጽ/ቤት ለወረዳችን እንስሳት ሕክምና ለመስክና ለቢሮ ህክምና ስራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዓይነት መድኃኒቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች።
- ሕጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላችሁ፣የ2014 ዓ.ም. ግብር ከፍላችሁ ፍቃዳችሁን ያሳደሳችሁ
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ፣
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላችሁ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆናችሁ፣
- የአቅራቢነት የምዝገባ የምስከር ወረቀት ያላችሁ፣
- የአገልግሎት ዘመናቸው ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት ማብቂያ ጊዜ ያላቸው ፣
- ከመድሐኒት ቁጥጥር ባለስልጣን እውቅና ያገኙ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ አቅራቢዎች
- ተጫራቾቹ ለጨረታ ማስከበሪያ ካስገቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችል።
- የጨረታ አሸናፊ ያሸነፉን መድኃኒቶች በራሱ ትራንስፖርት እስከ መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከወረዳው ታክስ አስተዳደር ደረሰኝ በመግዛት ከአ/ወ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመውሰድ ዋጋውን ሞልቶ ማቅረብ የሚችል።
- 1ተጫራቾች የሚጫረቱትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል ቴክኒካል ለብቻ፣ ቴክኒካል ፎቶ ኮፒ ለብቻ ይታሸጋል እንዲሁም ፋይናንሻል ለብቻ ፋይናንሻል ፎቶ ኮፒ ለብቻ በማድረግ በአንድ ትልቅ ፖስታ በሰም እንቨሎፕ በማሸግ አ/ወ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችል ሆኖ በፋይናንሻል ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት አይኖረውም።
- ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾቹ/ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾቹ በሰዓቱ መገኘት ባይችሉ ጨረታውን የጨረታ ኮሚቴው መክፈት የሚችል መሆኑን እየገለጽን
- ጽ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 224 0046
የአለታ ወንዶ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
