የአማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት በ2015 በጀት ዓመት ለቀላልና ከባድ ማሽነሪዎች እና ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የማሽነሪ ጎማ ፣ የቀላል እና ከባድ ተሽከርካሪ ጎማ እንዲሁም የተለያዩ Inner Tube ፣ hydraulic bottle jack ፣ Rime ፣ wire rop፣ Shera በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር AWWCE 03/2014
የአማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት በ2015 በጀት ዓመት ለቀላልና ከባድ ማሽነሪዎች እና ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውሉ
- የተለያዩ የማሽነሪ ጎማ፣
- የቀላል እና ከባድ ተሽከርካሪ ጎማ እንዲሁም
- የተለያዩ Inner Tube ፣
- hydraulic bottle jack ፣
- Rime ፣
- wire rop፣
- Shera በዘርፉ ተሰማርተው እየሰሩ ካሉ ሕጋዊ አቅራቢ ድርጅቶች መካከል በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ሕጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
- በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድና የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የተ.ዕ.ታክስ ምዝገባ ቁጥር እና የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱትን እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በመጫረቻ ቴክኒካል ሰነዳቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል።
- በአማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ስም የተሰራ በሲ.ፒ.ኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል /unconditional Bid bond/ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በዋጋ መሙያ ሰንጠረዡ ላይ ለተገለፁት ጎማዎች የሚያቀርቡትን ማስረጃዎችና የሚሞሉትን ዋጋ ኦሪጅናል እና ኮፒ ቴክኒካል ስፔስፊኬሽን በተናጠል ከሚያሳይ ብሮሸር ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የማቅረቢያ ጊዜያቸውን ውል በተያዘ ቢበዛ 60 ቀናት ውስጥ ማቅረብ የሚችል በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ማለትም የቴክኒክና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ኮፒ እና ኦሪጅናል በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 20 ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን አማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ቁጥር 32 በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ሰዓት ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ውል መፈረም ይኖርበታል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ሕጋዊ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በባንክ አካውንት ቁጥር 1000265163223 በመክፈል ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 በሚገኘው የድርጅቱ ህንፃ 3ኛ ፎቅ በምጣት መግዛት ይችላሉ።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን መሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ይህንንም በሚያደርግበት ጊዜ በድርጅቱ የማስታወቂያ መለጠፊያ ቦርድ እና በደብዳቤ ለተጫራቾች ያሳውቃል ነገር ግን ተጫራቾች ደብዳቤአቸውን እንዲወስዱ በስልክ አድራሻቸው ተነግሮ ካልወሰዱ እንደወሰዱ ይቆጠራል።
- ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉበትን ዕቃ ናሙና እንዲያቀርቡ በተጠየቁ ጊዜ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 226 52 03 ደወል ይችላሉ።
- አድራሻ ባህር ዳር ቀበሌ 14 ከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ ት/ቤት ጎን ወይም አዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፊት ለፊት
አማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት
