Tender Detail

Tender Details

  • Deadline12 Aug 2022, 11:24 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሳ ብሩ 1ኛ ደረጃ ቁጥር 1 ት/ቤት ለ2015 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ለKG (ቅድመ አንደኛ ደረጃ) ተማሪዎች የቤት ኪራይ እና የተለያዩ ጥገናዎች ማለትም የተማሪዎች መማሪያ ክፍል ግድግዳና ኮርኒስ ቀለም መቀባት የተሰባበሩ በር እና መስኮት ለማስጠገን ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 01/2015

በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሳ ብሩ 1ኛ ደረጃ ቁጥር1 ት/ቤት ለ2015 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ለKG (ቅድመ አንደኛ ደረጃ) ተማሪዎች የቤት ኪራይ ስለሚፈልግ እና የተለያዩ ጥገናዎች ማለትም የተማሪዎች መማሪያ ከፍል ግድግዳና ኮርኒስ ቀለም መቀባት የተሰባበሩ በር እና መስኮት ለማስጠገን ስለሚፈልግ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቅት፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፤ ቲን ነምበር እና አቅራቢ ዝርዝር ዉስጥ መመዝገብ አለባቸዉ።
  2. ለሎት1 (ለቤት አከራይ) የሚያስፈልጉ የቤት አከራይ ፍቃድ፤ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታና ቦታ ህጋዊ ሰነድ የግቢዉ ስፋት 2000 ካ.ሜ. እስከ 3000 ካ.ሜ. ስፋት ያለዉ፤ ለKG (ቅድመ አንደኛ ደረጃ) ተማሪዎች መማሪያ የሚሆን ክፍል 30 ክፍል ያለዉ፤ ቢሮ፤ የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ፤ የጥበቃ ቤት የተማሪዎች መጫወቻ ቦታ፤ በቂ ዉሃ፤ መብራትና ሽንት ቤት ያለዉ መሆን አለበት።
  3. ተጫራቾችይህንኑ የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውንይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እንቁላል ፋብሪካ እምቢልታ ሆቴል ከፍ ብሎ ከሚገኘው በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሳ ብሩ 1ኛ ደረጃ ቁጥር1 ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ስማችሁን ፊርማችሁና አድራሻችሁን ማስፈርና ማህተም በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሳ ብሩ 1ኛ ደረጃ ቁጥር ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛው ቀን 10፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ11ኛው ቀን በ3፡30 በጄኔራል ታደሳ ብሩ 1ኛ ደረጃ ቁጥር1 ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል።
  7. ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ተጫራቾች በሰነድ የሰጡት ዋጋ መለወጥ ማሻሻል ወይም ከውድድሩ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
  8. የማወዳደሪያ ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሞላት አለበት።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ ለሎት1 ብር 25,000 (ሀያ አምስት ሺ ብር ብቻ) ለሎት2 ብር 3000 (ሶስት ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተመሰከረለት CPO ብቻ ማቅረብ አለባቸዉ።
  10. መ/ቤቱ እንደአስፈላጊነቱ ከጥገናዉ ጠቅላላ ዋጋ 20% መጨመር ወይም 20% ከዉሉ በፊት መቀነስ የሚችል መሆኑን እንገልጻለን።
  11. መ/ቤቱ የሚያስጠግነዉን እስከ 6ወር ጥገናዉን ጠቅላላ ዋጋ 25% መጨመር ይችላል።
  12. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የዉል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።
  13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 827 8952
  • ማሳሰቢያ፡- በጨረታ የሚፈለገው የቤት ኪራይ በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 9 ውስጥ መሆን አለበት

በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሳ ብሩ 1ኛ ደረጃ ቁጥር1 ት/ቤት

Save Tender