የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት(አህሪ) ለስልጠና ክፍል የሚሆኑ እና ለላብራቶሪ ክፍል የሚሆኑ ፈርኒቸር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አህሪ/ብ/ግ/ጨ/013/2014 ዓ.ም.
የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት(አህሪ) ለስልጠና ክፍል የሚሆኑ እና ለላብራቶሪ ክፍል የሚሆኑ ፈርኒቸር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
የሚገዛው ግዥ (አገልግሎት) ዓይነት |
የጨረታ መለያ ቁጥር
|
ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን በብር |
|
ለስልጠና ክፍል የሚሆኑ ፈርኒቸር እና ለላብራቶሪ ክፍል የሚሆኑ ፈርኒቸር ግዥ |
አህሪ/ብ//ጨ/ 013/2014 ዓ.ም. |
15 ተከታታይ ቀናት
|
በሎት 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) ብቻ
|
ስለዚህ
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይንም ድረ-ገፅ መመዝገብ ይኖርባቸዋል ወይም በገንዘብ ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት እስከ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሠነድ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን በስራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀንና ሰዓት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኢንስቲትዩቱ የፋይናንስ እና ግዥ ዳይሬክቶሬት አለርት ግቢ ውስጥ አህሪ ተቋም መውሰድ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
- ኢንስቲትዩቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 011 369 9809/011 869 7217/011 321 1564/
የአማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት
(አህሪ)
