የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ የማሽነሪና የመኪና ጎማዎች እና የሰራተኛ ደንብ ልብሶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2014
የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከተማው ሴክተር መ/ቤቶች ለማዘጋጃ ቤቱ እና ለውክልና መ/ቤቶች ለ2015 በጀት ዓመት የሚውሉ የተለያዩ የማሽነሪና የመኪና ጎማዎች ፣ የሰራተኛ ደንብ ልብሶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ዝርዝር ሁኔታዎች
ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለዕቃዎቹ የሚገልፅ ሰነድ (ዶክመንት) የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ገፈርሣ ቡራዩ ክ/ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ያሳ ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ድረስ በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
የተጫራቾች ግዴታዎች
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ በስማቸው ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው እንዲሁም በፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በኦሮሚያ ገንዘብ ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በቡራዩ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው ሒሳብ ቁጥር 1000029292438 የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ ከቡራዩ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን በማስቆረጥ ከቡራዩ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰአት ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረ CPO (ሲፒኦ) 50,000.00 ብር ከጨረታ ሰነዱ ጋር የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ (ዋስትና 10%) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት በኦርጅናል እና በኮፒ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ የስራ ቀን እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 4:00 ሠዓት አድራሻ ቡራዩ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 107 ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4:00 ተዘግቶ በዕለቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች- (011 260 4879 ) ወይም (011 260 4836) በመደወል መረዳት ይችላሉ።
የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
ቡራዩ
