Tender Detail

Tender Details

  • Deadline16 Aug 2022, 10:37 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Chemicals And Reagents

በአማራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የደብረ ታቦር ጠቅላላ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተለያዩ ህትመቶች ፣ መድሃኒቶች እና የላብራቶሪ ሬጀንቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የደብረ ታቦር ጠቅላላ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ህትመቶች ፣ መድሃኒቶች እና የላብራቶሪ ሬጀንቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዝቅተኛ ዋጋ ከሞሉ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል።

1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ/የሥራ/ ፈቃድ ያላቸዉና ማቅረብ የሚችሉ።
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸዉ የከፋይ ማረጋገጫ የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያለቸዉና ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች የሚገዙትን ዕቃዎች ስፔስፍኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ/መ/ቤቱ በሚሰጣቸዉ መሰረት።
5. ተጫራቾች የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
6. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚፈለግባቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒዉን በጀርባዉ ላይ ከዋናዉ ጋር ተገናዝቧል ብሎ በመፃፍና ማህተም, ስም ፊርማና ቀን በማስቀመጥ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ።                                                                                                                 7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 20 (ሃያ ብር) ብቻ ከግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ዉስጥ መክፈል ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የዕቃዉን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመሂ-1 በመክፈል ማስያዝና ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በሲ.ፒ.ኦ ከሆነ ዋናዉ ሲ.ፒ.ኦ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
9. ማንኛውም ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላት አንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ፖስታዎች ኦርጂናል እና ኮፒ በማለት በአንድ ፖስታ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ላይ ስማቸውንና አድራሻቸውን በመፃፍ በደ/ታቦር ሆስፒታል ውስጥ ከግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሠዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን ፖስታውን እስከተገለፀው ቀን ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ውስጥ ጨረታው ይከፈታል። ነገር ግን 16ኛው ቀን የበዓል እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣ ሰዓት ይከፈታል።
10.በተጨማሪ ሲፒኦ /ጥሬ ገንዘብ እንዲያስይዙ ህግ የሚፈቅድላቸዉ ማህበራት ድርጅቶች ከጥቃቅን አነስተኛ ተቋም ለኢንስቲዩት በአድራሻየተፃፈ ማስረጃ ኮፒሰነድ ከነ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ጥቃቅን ለሆኑ ከተቋቋመ 5 አመት የሞላቸዉ ከሆነ የጨረታ ማስከበሪያ ሆነ የዉል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
11.የጨረታዉ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ማሻሻያ ማድረግ ወይም በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላትና የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኃላ ከዉድድሩ ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም።
12.ማንኛዉም ተጫራቾች መመሪያን ያልተከተለ አሰራር ሰርቶ የጨረታ ሂደቱን ካወከ ወይም ማሟላት ያለበትን በአግባቡ ካላሟላ ከጨረታዉ ይታገዳል፡፡አሸናፊዎች የሚለዩት በሚያቀርቡት ዝቅተኛ ዋጋ ብቻ ይሆናል።
13.አሸናፊዎች አሸናፊነታቸዉ እንደተገለፀላቸዉ ቅሬታ ከማቅረቢያ ጊዜ በተጨማሪ ባለዉ አምስት /5/ ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ሆ/ሉ ድረስ በመምጣት ዉል መዉሰድ ይኖርባቸዋል።
14.ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
15.አሸናፊዎች የዉል ማስከበሪያ አስር በመቶ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
16.ጨረታው ከመከፈቱ በፊት መቅረብ ያለበት ማስተካከያ ካለ ከ10 ቀናት በፊት ማቅረብ ይቻላል።
17.ተጫራቾች ሆ/ሉ አስፈላጊ ሁኖ ካገኘዉ አሸናፊዉን በጥቅል ድምር ሆነ በተናጥል የመለየት መብት ይኖረዋል። ነገር ግን በጥቅል ለመለየት የማይገደድ ይሆናል። መ/ቤቱ ቫትና ዊዝሆልድ ይቆርጣል።
18.ተጫራቾች የአሸነፋቸዉን ዕቃዎች ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ሁኖ ደ/ታቦር ሆስፒታል ድረስ በራሱ ወጭ ተሸፍኖ ማቅረብ አለባቸዉ።
19.ለበለጠ መረጃ ከግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስ.ቁጥር 0584411657/0920442225/0918195175 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
20.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

የደብረ ታቦር ጠቅላላ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

Save Tender