የአብክመ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የፍሪጅ የጥገና መለዋወጫ ዕቃዎችን እና ጤፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የአብክመ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት
- ሎት 1.የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የፍሪጅ የጥገና መለዋወጫ ዕቃዎችን
- ሎት 2. ጤፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።
- የግዥው መጠን 200,000( ሁለት መቶ ሺህ) በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ. 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ጀርባዉ ላይ ከዋናዉ ጋር ተገናዝቧል በማለት ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው
ማቅረብ አለባቸው። - ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ሃምሳ ብር (50 ብር) በመክፈል በኢንስቲትዩቱ ግቢ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ።
- የሚገዙ የዕቃዎችን/አገልግሎቶችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ከሐምሌ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በኢንስቲትዩቱ የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የፍሪጅ የጥገና መለዋወጫ ዕቃዎች ብር 5,000.00(አምስት ሺህ ብር) ለጤፍ ብር 25000 (ሃያ አምስት ሺህ ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በአካዳሚው ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በኢንስቲትዩቱ ግዥ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሐምሌ 18/2014 እስከ ነሀሴ 10/2014 ዓ.ም. 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወንም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ነሀሴ 10/2014 ዓ.ም. 4፡00 ታሽጎ 4:30 ይከፈታል።
- የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለዉም።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582 26 23 60 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የአብክመ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት
