የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የመኪና መለዋዎጫ እቃዎች ዓመታዊ ውል (ኮንትራት) ግዥ እና የመኪናዎች ሞተር ዘይት ግዥ መግዛት ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በማእከላዊ ጎንደር ዞን መስተዳድር ውስጥ የሚገኘው የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለባለበጀት ሴክተር መ/ቤቶች ከሎት 1 እስከ ሎት 2 ያሉትን ዝርዝር ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የመኪና መለዋወጫዉን ዓመታዊ ዉል/ኮንትራት/መግዛት እና የሞተር ዘይት ግዥ ግን በአንዴ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 ፡- የመኪና መለዋዎጫ እቃዎች ዓመታዊ ዉል/ኮንትራት/ ግዥ
- ሎት 2 ፡- የመኪናዎች ሞተር ዘይት ግዥ፣
ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ከሆኑ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።
- የጨረታ ዋጋው ከብር 200,000 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የሚወዳደሩት ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚያስፈልጋቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሎት 1 እስከ ሎት 2 ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ብር) ከ25/11/20114 ዓ.ም እስከ 10/12/2014 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ድረስ ቢሮ ቁጥር 7 መግዛት እና ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡ በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ከሆነ የገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ኮፒ በማድረግ ኮፒውን ከኦርጅናሉ ሰነድ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታዉ በ11/12/2014 ዓ.ም የጨረታ ሳጥኑ ከጠዋቱ 3፡46 ታሽጎ 4፡00 ላይ ይከፈታል።
- የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ በለሉበት ሰነዱ ተሟልቶ ከተገኘ ይከፈታል። ሆኖም ግን ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኝ የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉለው ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለተላለፉ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ።
- በጨረታ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ቅድመ ክፍያ መውሰድ የሚፈልግ ከሆነ በሚወስደው የቅድመ ክፍያ የገንዘብ መጠን ተመጣጣኝ የቅድመ ክፍያ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- በጨረታ አሸናፊው ድርጅት የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 25 በመቶ የውል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ አለበት።
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከጽ/ቤቱ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583320175 ወይም 0583320013 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
