የባህርዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት መሸጥ ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የባህርዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት መሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫረታቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል።
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሚሸጡ ያገለገሉ ንብረቶችን
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣
- የፅህፈት እቃዎች ፣
- የተሽከርካሪ ጎማዎች ከነካላማዳሪያቸው ፣
- የኃላፊና ፅሃፊ ወንበሮች እና ሲንኮችን መሸጥ ይፈልጋል።
- የሚሸጡ ያገለገሉ ንብረቶች አይነትና ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) ብቻ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ብር ከሽያጩ ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ የገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኝን ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተጫራቾች ማስያዝ አለባችሁ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአገልግሎቱ በግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት የመጫረቻ ሰነዱን በመግዛት እና እስከ 16ኛው ቀን 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችሁ በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 04 በ16 ቀን 2014 ዓ/ም 3፡10 ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ዕለት 3፡30 ይከፈታል።
- በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582 20 07 71/0582 22 22 10 በመደወል ማግኘት
ይችላሉ። - ለሽያጭ የሚቀርቡ ንብረቶች ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ በተገለጸው ቦታ (ከተማ) ጨረታው ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ
15 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ 11፡30 ንብረቶችን ባሉበት ቦታ ድረስ በመሄድ ማየት ይችላሉ። - የጨረታው አሸናፊዎች በገቡበት ውል መሰረት ያሸነፉበትን የንብረቶች ዋጋ ብር 100 በመቶ ውሉን ከፈረሙበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ/መቤቱ
አካውንት ቁጥር ወይም በመ/ቤቱ ዋና ገንዘብ ያዥ በቢሮ ቁጥር 05 ገቢ ማድረግ አለባቸው። - በጨረታው ያሸነፉ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ንበረቶች የሚረከቡበት ንብረቶች በተቀመጡበት መ/ቤት /ሻጭ መ/ቤት በሚጠቅሰው ቦታ ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የባ/ዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
