Tender Detail

Tender Details

  • Deadline23 Sep 2022, 1:54 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ምግብ እና ተያያዥ ግብዓቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁፕር፤ AAU/COBE/Mg/NCB/01/2014

  • ሎት: 1 የጤፍ ዱቄት፣ ዳቦ፣ዳቦ ቆሎ፣ቆሎ ገብስ እና ኩኪስ
  • ሎት2፡ የፋብሪካ ውጤቶች
  • ሎት3: ጥራጥሬ (ባልትና ውጤቶቾ) እና ቅመማ ቅመም
  • ሎት4፡ እንሰሳት ተዋጽኦ
  • ሎት 5 አትክልትና ፍራፍሬ
  • ሎት 6- የታሸገ ውሃና
  • ሎት 7:- ከሰልና እንጨት ግዥ ጨረታ
  1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በሎት ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ምግብ እና ተያያዥ ግብዓቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
  2. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ከዚህ በላይ በሎት የተጠቀሱትን የምግብ እና ተያያዥ ግብዓቶች ለማቅረብ ብቃት ያላችሁ ድርጅቶች በታሸ ኢንቬሎፕ የጨረታ ሰነድ እንድታቀርቡ ተጋብዛችኋል፡፡
  3. ጨረታዉ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት የመንግሥት ግዥ አዋጅ በተገለጸው ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ሥነ-ሥርዓት መሠረት ይፈጸማል፡፡ የምግብ እና ተያያዥ ግብዓቶች ግዥ ጨረታ የሚከናወነው ብቁ ከሆነ ተጫራች እና ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ የ2014 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፤ የዘመኑ ግብር መክፈላቸውን የሚገልጽ ወቅታዊ ደብዳቤ ከአገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውሰጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ዌብሳይት ላይ ፕሪንት አርጋችሁ እንዲሁም ቲን ሰርተፍኬት ኮፒውን ማቅረብ የሚችል ይሆናል፡፡ ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ካደራጃቸው አካል ደብዳቤ በማጻፍና በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን በነጻ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ከዚህ በታች በቁጥር 7(ሀ) በተገለፀው አድራሻ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባን ሒሳብ ቁጥር 1000087400078 ከፍለው ደረሰኝ በማምጣት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጨምሮ በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 (A) በተገለጸው አድራሻ ነሀሴ 17 ቀን 2014 ዓ.ም. አስከ 8:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው በተጫራቾች መመሪያ በተዘረዘረው መሠረት አያይዘው ያቀርባሉ፡፡ ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ በጨረታው ላይ ለመገኘት የፈለጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቁጥር 7 (ሐ) በተጠቀሰው አድራሻ ነሀሴ 17 ቀን 2014 ዓ.ም. በ8:30 ሰዓት ይከፈታል::በተጨማሪም ለቀረቡት የምግብ እና ተያያዥ ግብዓቶች ግዥ ጨረታ ሳፕል ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 (ለ) በተገለጸው አድራሻ ነሀሴ 17 ቀን 2014 ዓ.ም በ8:00 ሰዓት ወይም በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታ ሠነዱን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚከስ ኮሌጅ ከጨረታ መከፈቻ ጊዜ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን በሚከተለው ሰንጠረዥ ውስጥ

ተቁ

ሎቶች

የጨረታ ዋስትና ብር
መጠን

 

ብር

 

ሣ

1

የጤፍ ዱቄት፣ዳቦ፣ዳቦ ቆሎ፣ቆሎ ገብስ እና ኩኪስ

10,000

00

2

የፋብሪካ ውጤቶች

10,000

00

3

የእንሰሳት ተዋጽዖ

10,000

00

4

ጥራጥሬ( የባልትና ውጤቶች) ቅመም እና ቅመማ

10,000

00

ተ.ቁ
 

ሎቶች

የጨረታ ዋስትና ብር
መጠን

ብር

ሣ

5

አትክልትና ፍራፍሬ

10,000

00

6

የጽዳት ዕቃዎች

5,000

00

7

የታሸገ ውሃ 1/2 ሊትር እና 1 ሊትር

10,000

00

8

ከሰልና እንጨት

5,000

00

በተቀመጠው መሰረት ለሚወዳደሩበት ሎት የተገለጸውን የገንዘብ መጠን በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

7. ሀ/ ሰነዶቹ የሚወጡበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚhስ ኮሌጅ ላይብረሪው ፊት ለፊት ያለው ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 001 ይሆናል፡፡ ጨረታው ነሐሴ 17 ቀን 2014 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጅ ግዥ ክፍል ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡

8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ማብራሪያ ስልክ ቁፕር 0111 260 568/0111 542 227

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ

Save Tender