Tender Detail

Tender Details

  • Deadline14 Aug 2022, 12:33 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Chemicals And Reagents

የሚዛን ቴፒ ዩንቨርስቲ ማስተማሪያ ሆስፒታልና ጤና ሳይንስና ህክምና ኮሌጅ የሠው ህክምና መድሃኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንት ፣ የጽህፈት መሳሪያ ፣ የጽዳት ዕቃዎች ፣ የደንብ ልብስ ፣ የህትመት ፣ የመኪና ጎማ ግዥና የኤሌትሪክ ፣ የውሃ ዕቃዎችና የህንጻ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

የሚዛን ቴፒ ዩንቨርስቲ ማስተማሪያ ሆስፒታልና ጤና ሳይንስና ህክምና ኮሌጅ ከዚህ በታች የተገለፁት፡የሠው ህክምና መድሃኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንት ግዥ ፣ የጽህፈት መሳሪያ ግዥ ፣ የጽዳት ዕቃዎች ግዥ ፣ የደንብ ልብስ ግዥ ፣ የህትመት ግዥ ፣ የመኪና ጎማ ግዥና የኤሌትሪክ ፣ የውሃ ዕቃዎችና የህንጻ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት1 የሠው ህከምና መድሃኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንት ግዥ፤
  • ሎት2 የጽህፈት መሳሪያ ግዥ፤
  • ሎት3 የጽዳት ዕቃዎች ግዥ፤
  • ሎት4 የደንብ ልብስ ግዥ፤
  • ሎት5 የህትመት ግዥ፤
  • ሎት6 የመኪና ጎማ ግዥ፤
  • ሎት7 የኤሌትሪክ፣የውሃ ዕቃዎችና የህንጻ ዕቃዎች ግዥ፤

ስለሆነም ማንኛውም በዘርፉ አገልግሎት ሰጪ የተሰማሩ በውድድሩ ላይ እንዲካፈሉ እየጋበዝን በውድድሩ ላይ ለመካፈል ቀጥሎ የቀረቡትን መመዘኛዎች ወይም መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1.  በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ ምhር ወረቀት፣ የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀትና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት አለበለዚያ መ/ቤቱ የተሞላውን ዋጋ ከነቫቱ አድርጎ ነው የሚወስደው።
  3. የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 / አስራ አምስት/ የስራ ቀናት ውስ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመhፈል የሚዛን ቴፒ ዩንቨርስቲ ቲቺንግ ሆስፒታል ከግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 እና በአዲስ አበባ ኣሜሪካን ኢንባሲ ፊትለፊት ከሚገኘው የሚዛን ቴፒ ዩንቨርስቲ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የፋይናንሻል መገምገሚያ ስፈርት መ/ቤቱ በሚያዘጋጀው በዋጋ ማቅረቢያ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በመሙላት ተፈርሞበት የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ/ ፖስታ ኦርጂናልና ኮፒውን ለብቻ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የቴከኒካል መገምገሚያ ለብቻው ተፈርሞበት የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ/ፖስታ ኦርጂናልና ኮፒውን ለብቻ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ለሁሉም ሎቶች ናሙና በዓይነት መቅረብ የሚችሉትን በአይነት አልያም በአይነት መቅረብ የማይችሉትን በካተሎግ (በፎቶ ግራፍ ከዝርዝር መግለጫ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለባቸው።
  7. አሸናፊ ሆኖ የሚረጠው ድርጅት በግዥ ትዕዛዝ የሚሰጠውን ንብረት የማስተማሪያ ሆስፒታል መጋዘን ድረስ በራሱ ትራንስፖርትና ወጪ የማጓጓዝና በራሱ የጉልበት ሠራተኛ የማስገባት ግዴታ አለበት።
  8. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በባን በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ቢድ ቦንድ 50,000ብር/ሃምሳ ሺ ብር/ በፖስታ ለብቻው በማሸግ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው ተከታይ 15 የስራ ቀናት ይቆይና በ15ኛ ቀን 11:00 ሠዓት ላይ ታሽጎ በ16ኛ ቀን ከሠዓቱ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የሚከፈትበት ቀን ዝግ ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።
  10. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በዕሁፍ ከተገለፀለት በኋላ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ለውል ማስከበሪያ የግዥውን 10% በባን በተሰከረ CPO በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም አለበት ውሉን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ባይገባ /ባይፈጸም/ የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  11. ተጫራቾች እያንዳንዳቸው የሚወዳደሩበት ጨረታ የእቃውን ዝርዝር በሠነዱ ላይ ያለውን ብቻ መሠረት ማድረግ ይኖርባቸዋል።
  12. መ/ቤቱ የግዥ መጠን 20% ከፍ ወይም ዝቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታ ን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ- ሚዛን ቴፒ ዩንቨርስቲ ቲቺንግ ሆስፒታል ስል ቁጥር 047 336 0770

የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቲቺንግ ሆስፒታል

 

Save Tender