የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ አልባሳት ፣ የተሽከሪካሪ መለዋወጫዎች ፣ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ፣ ኮስሞቲክስ ዕቃዎች ፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣ የህንፃ መሣሪያዎች እና ሞተር ሳይክሎችን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
ቁጥር 09/2012
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ
- አልባሳት ፣
- የተሽከሪካሪ መለዋወጫዎች ፣
- ልዩ ልዩ ዕቃዎች ፣
- ኮስሞቲክስ ዕቃዎች ፣
- ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣
- የህንፃ መሣሪያዎች እና
- ሞተር ሳይክሎችን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የግልጽ ጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00- 12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በጽ/ቤታችን የዕለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ ቁጥር 16 በመገኘት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊያው ቀን ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- በግልጽ ጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) በጉምሩክ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫፍ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚካሄደው በሞያሌ ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ባሉበት ወይም ታዛቢ ፊት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እስከ 7ተኛው ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም መ/ጣቢያ የሚገኙ መጋዘኖቻችን እየሄዱ መመልከት ይችላሉ።
- ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 3፡45 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ) ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት (አራት ሰዓት) ላይ ይከፈታል።
- ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው መሰረት ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 8ኛው ቀን የሥራ ቀን ሳይሆን ቢቀር የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
- ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ. (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለጸ በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
- ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው CPO ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0464 44 03 83/0464 44 03 75/0464 44 15 64 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
