Tender Detail

Tender Details

  • Deadline14 Aug 2022, 10:58 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Tour And Travel

የአዳማ ገቢዎች ሚኒስቴር ቅ/ፅ/ቤት ለሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት 30 ሰው የመጫን አቅም ያላቸው ሶስት ተሽከርካሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2015

የአዳማ ገቢዎች ሚኒስቴር ቅ/ፅ/ቤት ለሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት 30 ሰው የመጫን አቅም ያላቸው ሶስት ተሽከርካሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።

 ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

  1. አገልግሎቱ የሚሸፍነው ቦታ በአዳማ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ሲሆን ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል።
  2. ተጫራቾች በስራ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣ እንዲሁም የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉና ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የድጋፍ ደብዳቤ ከሚመለከተው የገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  3. አንድ ተጫራች የራሱ የሆኑ ሶስት አውቶቢሶችን ማቅረብ የሚችል ወይም ከአንድ የትራንስፖርት ማህበር ከሆነ ሶስት አውቶቢሶችን ማቅረብ መቻል አለበት።
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለት 15 ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ሳር ተራ አካባቢ በሚገኘው የአዳማ ገቢዎች ሚኒስቴር ቅ/ፅ/ቤት ኦሮሚያ ባንክ ዲስትሪክት ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 05 መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 በፊት ለጨረታው የሚያስፈልግ ማንኛውንም የጨረታ ሰነድ በቅ/ጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው። በመሆኑም የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  6. የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባለበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ታሽጎ ከጠዋቱ 3:45 ይከፈታል። ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ይከፈታል።
  7. ማንኛውም ተጫራች ለሁሉም ተሽከርካሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ በጠቅላላ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ የተመሰከረለት ቼክ (ሲ.ፒ.ኦ.) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ በአዳማ ገቢዎች ሚኒስቴር ቅ/ጽ/ት ስም አሰርተው ማቅረብ አለባቸው።
  8. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +25122 21 40 10 ፣ +25122 21 34 73 እና +25122 21 16 80 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የአዳማ ገቢዎች ሚኒስቴር ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender