የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅጽ/ቤት የመገናኛ መሣሪያዎች፤ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ፣ የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች ፣ የመኪና መለዋወጫዎች የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ እና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2015
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተዉና ተወርሰው የሚገኙ
- የመገናኛ መሣሪያዎች፣
- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
- የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች፣
- የመኪና መለዋወጫዎች፣
- የትራክተር መለዋወጫዎች እና
- ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ እና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- ተሽከርካሪዎች ላይ መወዳደር የሚፈልግ ተጫራች ማንኛውም እድሜው ከ18 ዓት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ መወዳደር ይችላል።
- የግልጽ ጨረታ ተሳታፊ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለውያላት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ሲሆን ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 መቶ ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡oo እስከ 6፡oo፣ ከሰዓት ከ7፡oo እስከ 11፡oo ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ2፡oo እስከ 6፡oo ሰዓት ድረስ ብቻ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ ከገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
- ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበት ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንh የተመሰከረለትን C.P.O የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመhፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል። ማንኛውም የሃራጅ ጨረታ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ለትራክተር መለዋወጫ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንh የተመሰከረለትን C.P.O ማቅረብ ይኖርበታል።
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው (ስድስተኛው) ቀን የግልፅ ጨረታ ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡05 የሚከፈት ሲሆን ሃራጅ ጨረታ 4፡30 በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ይጀመራል። ነገር ግን ጨረታው በበዓል/እሁድቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት የሚቀጥለው የስራ ቀናት ይሆናል።
- ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦታ ከነ ቫት እና ያለቫት በሚል በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልh በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ ወይም ፖስታ መቅረብ አለባቸው ። ከዚህ ሰነድ ውጭ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ለመቀበል አይገደድም።
- ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋና መግለጫ መለወጥ እና ማሻሻል አይችልም።
- ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም።
- በጨረታውለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል።
- ተጫራቾች ዕቃውን ሳያዩ ዋጋ ቢሰጡና ችግር ቢፈጠር ባለስልጣኑ ተጠያቂ አይሆንም።
- ለጨረታው የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ ነው።
- አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ይሆናል።
- ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡-046 212 5396
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት
