Tender Detail

Tender Details

  • Deadline11 Aug 2022, 10:48 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Equipment And Accessories

ኢትዮጵያ ቆዳ አክሲዮን ማህበር ያገለገሉ ብረታ ብረቶች ፣ አሮጌ የኤሌክትሪክ ሞተሮችን ፣ የማሽን ምላጮችን ፣ አሮጌ የጣሪያ ክዳን ቆርቆሮዎችን ፣ የተለያዩ የፕላስቲክና ጎማ ቱቦዎችን ፣ የመስታወት ስብርባሪዎችን እና ያገለገሉ የእንጨት ውጤቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


ያገለገሉ ብረታ ብረቶች ሽያጭ

ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2014

ኩባንያችን ያገለገሉ ብረታ ብረቶች ፣ አሮጌ የኤሌክትሪክ ሞተሮችን ፣ የማሽን ምላጮችን ፣ አሮጌ የጣሪያ ክዳን ቆርቆሮዎችን ፣ የተለያዩ የፕላስቲክና ጎማ ቱቦዎችን ፣ የመስታወት ስብርባሪዎችን እና ያገለገሉ የእንጨት ውጤቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተመለከቱትን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲካፈሉ ይጋብዛል።

  1. የሚሸጡትን ያገለገሉ ንብረቶች ዘወትር በሥራ ቀናት ከቀኑ 4፡00-10:00 ሰዓት ድረስ ሞጆ ኤጀርሣ በሚገኘው ፋብሪካ ግቢ ውስጥ በአካል በመመልከት የሚገዙበትን ዋጋ በግልጽ በሚነበብ ጽሑፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ለጨረታው የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ከኩባንያው ፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
  2. በግልጽ የማይነበቡና ስርዝ ድልዝ ያለባቸው የጨረታ ሠነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።ተጫራቾች ባሸነፉበት ዕቃ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ጨምረው ይከፍላሉ። ሌላ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት ተቀባይነት አያገኝም።
  3.  ለሚገዙት ብረታ ብረት ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. አሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና ይያዛል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሠነዳቸውን ነሐሴ 05 ቀን 2014 ዓ.ም. ከረፋዱ በ4:00 ሰዓት አዲስ አበባ ካዲስኮ አደባባይ አጠገብ በሚገኘው የኩባንያው ቅርንጫፍ መ/ቤት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. አሸናፊው ተጫራች የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ በ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን ዕቃ ሙሉ ዋጋ ከፍሎ ማንሳት ይኖርበታል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልተነሳ ጨረታው ውድቅ ተደርጐ የተያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለኩባንያው ገቢ ይሆናል። አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርትና ሠራተኛ ያጓጉዛል።
  7. ጨረታው ነሐሴ 05 ቀን 2014 ዓ.ም. ከላይ በተራ ቁጥር 7 በተመለከተው ቦታ ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ይካሄዳል።

ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011 470 8191, 022 111 3333

ኢትዮጵያ ቆዳ አክሲዮን ማህበር

Save Tender