ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የፋይናንሻል ኦዲት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በጨረታ ቁጥር SMTSE/ኦዲ/ግጨ/16/2014/2022
ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በሰንጠረዥ የተገለፁ የፋይናንሻል ኦዲት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ. |
የሚገዛው እቃ (አገልግሎት) አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
የጨረታ መለያ ቁጥር
|
የጨረታ ሰነድ መመለሻ ቀን
|
የጨረታ ሰነድ መክፈቻ ቀን
|
|
1 |
የፋይናንሻል ኦዲት አገልግሎት |
ብር 30,000
|
SMTSE/ኦዲ/ግጨ/16/2014/2022 |
ነሀሴ 07/2014 ዓ.ም. ከሰዓት 8:00 |
ነሀሴ 07/2014 ዓ.ም. ከሰዓት 8:30 |
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራቾች፡
- ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውንና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ወቅታዊ ደብዳቤ(Tax Clearance) በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት (VAT Registration) እና የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፊኬት (TIN Certificate) ማቅረብ አለበት።
- ከክልል ወይም ከፌዴራል መ/ቤት ቢሮ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመያዝ 22 እየሩስ ህንጻ ፣ 7ኛ ፎቅ ፣ ሸገር የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የግዥና ንብ/አስተ/ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7-07 መውሰድ የሚችሉ ሆኖ የጨረታው ሰነድም በዚሁ አድራሻ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች በሰንጠረዡ በተገለጸው የብር መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ከህጋዊነት ማረጋገጫ ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰነዶች ጋር በሲፒኦ ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ዋስትና በማስያዝ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከወሰዱበት ቀን ጀምሮ በተራ ቁጥር 2 በተገለፀው አድራሻ ከላይ በሰንጠረዥ በተገለጸው ቀን ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ የሚከፈት ሲሆን ዘግይቶ የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዳቸው ሎቶች የታሸገ አራት ኤንቨሎፕ (ቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ) ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ ፖስታዎቹ ላይ መገለጽ አለበት።
- የሸገር የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ጨረታውን የሚመለከት መረጃ በስ.ቁ. 011 863 9877/011 833 4076 ማግኘት ይችላሉ።
ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት
