ጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባድ የተያዘ ነጭ ጋዝ ተለክቶ የሚወሰድ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጉምሩክኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባድ የተያዘ ነጭ ጋዝ ተለክቶ የሚወሰድ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ለጨረታ የቀረበን ጋዝ ከ 25/11/2014 ጀምሮ በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት ወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል።
በጨረታው ላይ መካፈል ለሚፈልጉ ተጫራቾ
- የዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያለው እና የዘመኑን ግብር የከፈለ እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒ.ኦ /CPO| ለግልፅ ጨረታ የመጫረቻውን 50,000 (ሃምሳ ሺ ብር) ማስያዝ የሚችል ፤
- ለግልፅ ጨረታ ቅ/ፅ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቹ በጨረታ አሸንፎ የገዛውን ነጭጋዝ ወዲያኑ ከፍለው በ05 ቀን የሚረከብ ሆን አለበት
- ጋዙን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲውኑ ከፍለው በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከ በያስዘው ሲ.ፒኦ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
- ጨረታው ያላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያኑ ይመለስላቸዋ።
- ማንኛውም ተጫራች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ አሰርቶ ማምጣት አለበት።
- አሳማኝ የሆነ ምከንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል።
- ማንኛውም ተጫራቾ ጋዙን ካሸነፉ በኃላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል።
- ተጫራቹ ጋዙን አሸንፎ ከተረከበ በኃላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።
- ተጫራች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ ሐምሌ 28/11/2014 ዓ.ም ከጥዋቱ 2፡00 እስከ 3:45 በጅግጅጋ ጉ/ኮ ቅ/ጽ/ቤት በተዘጋጀ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ጨረታ 3፡45 ተዘግቶ በ 28/11/2014 ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
ጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት
