በደ/ብ/ብ/ሕ/ከ/መንግስት በጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ ፋ/ል/ጽ/ቤት የመንገድ መብራት ዝርጋታ ስራ ለማሠራት ይፈልጋል
የጋልማ ከተማ ማዘጋጃ ቤ/አገ/ጽ/ቤት የመንገድ መብራት ጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ሕ/ከ/መንግስት በጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ ፋ/ል/ጽ/ቤት የመንገድ መብራት ዝርጋታ ስራ ለማሠራት ይፈልጋል። በዚህ መሠረት በኤሌክትሮካኒካል ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ፈቃድ ያላቸውና ፈቃዳቸውን ለ2014 ዓ.ም. ያሳደሱ በጨረታ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
በዚህ መሰረት የዛላ ወረዳ ፋ/ል/ጽ/ቤት ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውና መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በሰንጠረዡ ውስጥ የተመለከተውን ዝርዝር ተከትለው የመንገድ መብራት ዝርጋታ ሥራ ለመሥራት በጨረታው እንዲወዳድሩ ይጋብዛል።
|
ተ.ቁ |
ፕሮጀክቱ የሚሠራበት ሣይት |
ምርመራ |
|
1 |
የመንገድ መብራት ዝርጋታ ከወረዳ አስተዳደር እስከ ንግድ ባንክ እና ከአደባባይ እስከ ጥምቀተ ባሕር |
አንድ ጨረታ
|
- ጨረታው በአገራዊ ግልጽ ጨረታ የሚታወጅ ሲሆን ሁሉም ሕጋዊ የሆኑ የአገር ውስጥ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ በጨረታ ሠነዱ ላይ ተካትቷል።
- ሁሉም ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፋይናንስ ልማት ጽ/ቤት በሚከተለው አድራሻ መሠረት ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪም ከሠነዱ በቂ መረጃዎችን ማንበብ ይችላሉ በተጨማሪም በማንኛውም የሥራ ቀን ከተዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 እና ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡30 ማግኘት ይችላሉ።
- መገምገሚያ መስፈርቶች፡- ሕጋዊ መሰፈርቶች ፣ቴክኒካል መስፈርቶች እና ፋይናንሻል መስፈርቶች ሆኖ ዝርዝር መስፈርቶች በጨረታ ሠነድ ተካትቷል። በተጨማሪ ተጫራቾች ሕጋዊ የመጫረቻ ሠነዶችን ለውድድሩ ያቀርባሉ።
- የተሟላ የጨረታ ሠነዱ የተዘጋጀው በእንግሊዘኛ ሆኖ ሕጋዊ ተጫራቾች ሠነዱን መግዛት የሚፈልጉ ማመልከቻ በሜዝ በገቢዎች ጽ/ቤት ለሠነድ መግዣ 500 ብር (አምስት መቶ ብር ብቻ) ገቢ በማድረግ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሠነዶች ይህ ጨረታ ከሚከፈትበት ከ22 ቀን በፊት በዛላ ወረዳ ፋ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ተዘጋጅቶ የሚቀመጥ ሲሆን ማንኛወም ተጫራች ጨረታው ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ወደ ዛላ ወረዳ ፋ/ል/ጽ/ቤት ከላይ በተራ ቁጥር-2 በተገለጸው የሥራ ሰዓት ቀርቦ መግዛት ይችላል።
- የጨረታው አስተሻሸግ በአንድ ፖስታ ስርዓት ሲሆን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሠነዶች ኦሪጅናል በአንድ ፖስታ በአንድ ላይ ታሽጎ በላዩ ላይ “ኦርጂናል” ተብሎ ተጽፎ እና ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሠነዶች ኮፒ በአንድ ፖስታ በአንድ ላይ ታሽጎ በላዩ ላይ “ኮፒ” ተብሎ ተጽፎ በአንድ እናት ፖታ ታሽጎ መቅረብ አለበ።
- ይህ ጨረታ የሚከፈተው ጨረታው ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉ 21 ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ22ኛው ቀን ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ሲሆን የጨረታ መክፈቻ ቀን በሳምንቱ መጨረሻ ቀን ወይም በበዓል ቀን የሚሆን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ በ4፡30 ይከፈታል፡፡ የተጫራች ወይም የሕጋዊ ወኪል ለመአገኘት የጨረታውን መከፈት አይከለክልም።
- ሁሉም ተጫራቾ የጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 ብር (ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ) በሕጋዊ ዋስትና ሠነድ ማስያዝ አለበት።
- ተጫራቾች በደቡብ ክልል በተሻሻለ በ2010 ዓ.ም. የግዥ መመሪያ መሰረት አንቀጸው 16.19.2.1 መሠረት ማንኛውንም የሂሳብ ስህተት ከ2% በላይ ዝቅ ወይም ከፍ ካለ ከጨረታ ውጪ እንደሚደረግና የሂሳብ ስሌት ማስተካከያውን አምኖ ለመቀበል ፈቃደኛ መሆን አለበት።
- መሥራት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ከውል በፊት ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ የሚከተሉትን መረጃዎች ይጠቀሙ።
|
ተ.ቁ |
የሥራ ሂደት |
ተወካይ |
ስልክ |
|
1 |
የግዢ ሥራ ሂደት ኃላፊ |
አብደላ እንድሪስ |
0913 07 46 50 |
|
2 |
ጋልማ ከተማ ማዘጋጃ ቤ/አገ/ጽ/ቤት |
አመኑ እንዱቆ |
0916 474 3 19 |
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በጎፋ ዞን የዛላ ወረዳ ፋ/ል/ጽ/ቤት
