የገላን ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የመኪና እና ማሽነሪ ጎማዎች እና ከመነዳሪያዎች ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የገላን ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2015 የበጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ፡-
- የመኪና እና ማሽነሪ ጎማዎች እና ከመነዳሪያዎች ለመግዛት ስለሚፈልግ
ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ (መረጃዎች በማቅረብ) ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡ ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የሥራ ቀናት ሰነድ የማይመለስ ብር 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ) ብር በገላን ከተማ ገቢዎች ባለሥልጣን ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ከገላን ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር (ሰነድ) ዋና እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ (በፖስታ) በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የሥራ ቀናት በገላን ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ባዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ (ተዘግቶ) ልክ በዚሁ ቀኑ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገላን ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊነቱ ከተለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ የጨረታ ማስከበሪያቸው ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- ጥራት (Quality) በሌለው ጎማ ላይ (በኢትዮጵያ ደረጃ መዳቢዎች በተሰጠ መስፈርት (Standard) በታች የሚያቀርቡ ተጫራቾች መስሪያ ቤቱ የማይደራደር መሆኑን በቅድሚያ ያሳውቃል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ፣ ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለው ማለት አይችልም።
- የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዱ በተዘረዘረው መሠረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 445 0182 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ገላን ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት
