አማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ስድስት የላፕቶፕ ኮምፒውተር ፣ አንድ ዴስክ ቶኘ ኮምፒውተር እና አንድ ፕሪንተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ኤሌክትሮኒክስ ግዥ መግዛት ይፈልጋል
የኤሌክትሮኒክስ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
አማራ ልማት ማህበር /አልማ/ የክልሉን ህዝብና የልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት የማንቀሳቀስ በትምህርት፣ በጤና እና የስራ እድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋፅኦ የማድረግ ተልዕኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሃገር በቀል የልማት ማህበር ነው፡፡ አማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ከPRESERVE FH ጋር በመተባበር ለምናከናውነው ፕሮጀክት
- ስድስት የላፕቶፕ ኮምፒውተር ፣
- አንድ ዴስክ ቶኘ ኮምፒውተር እና
- አንድ ፕሪንተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ኤሌክትሮኒክስ ግዥ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር ብቻ) በመክፈል በማህበሩ ዋናው ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 108 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የእቃው ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከቢሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች መረጃውን በትክክል በመሙላት፣ ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች መሠረት በማድረግ የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነዶች ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ሰነዶችን ለመለየት እንዲቻል በግልጽ ፅሁፍ ኤንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በአማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ዋናው መ/ቤት ባህር ዳር ቢሮ ቁጥር 100 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን 8፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በእለቱ በ9፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጀ ከፈለጉ በማህበሩ ዋናው ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 100 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583207360 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ልማት ማህበር /አልማ/
