የአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኤሌክትሪክ ጥገና ፣ የዉሀ መስመር ጥገና እና የእንጨትና ብረታ ብረት ዉጤቶች (የቢሮ ቁሳቁስ) ጥገና እና የህትመት ስራ ዓመታዊ ዉል ይዞ ተጫራቾችን በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኤሌክትሪክ ጥገና ፣ የዉሀ መስመር ጥገና እና የእንጨትና ብረታ ብረት ዉጤቶች /የቢሮ ቁሳቁስ/ ጥገና እና የህትመት ስራ ዓመታዊ ዉል ይዞ ተጫራቾችን በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
- በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያለውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል፣ እንዲሁም ህጋዊና ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ያሣተመ፣
- ለዚህ የተዘጋጀውን ሠነድ ቢሮ ቁጥር 09 በአካል በመቅረብ በብር 30/ሰላሳ ብር/ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ሠነድ ያለምንም ስርዝ ድልዝ መሞላት ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ዋጋ በመሆኑ ሁሉም ዝርዝሮች መሞላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለኤሌክትሪክ ጥገና 1000 /አንድ ሽህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለዉሀ መስመር ጥገና 500/አምስት መቶ ብር/ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የእንጨትና ብረታ ብረት ዉጤቶች /የቢሮ ቁሳቁስ/ ጥገና /1000/አንድ ሽህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለህትመት 1580/አንድ ሽህ አምስት መቶ ሰማንያ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዛቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ከሠነድ ጋር አብሮ አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡
- የተሞላው ዋጋ ቫትን የሚጨምር ወይም የማይጨምር መሆኑ መግለፅ ይኖርበታል፡፡ የተገለፀ ነገር ከሌለው ከቫት ጋር እንደተሞላ ይቆጠራል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ተኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡30 ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታዉን ለመክፈት የሚያግድ ነገር አይኖርም፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በአካል ቢሮ ቁጥር 013 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0582262719/0582205269 ደውሎ
መጠየቅ ይችላሉ፡፡ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት
