Tender Detail

Tender Details

  • Deadline04 Sep 2022, 6:18 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Water System Installation

ሴንድ ኤ ካዉ ኢትዮጵያ በወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጉሩሞ ውይዴ ቀበሌ አንድ የንጹህ መጠጥ ውሃ ምንጭ የማጎልበት ሥራ ለማሰራት ይፈልጋል


ለምንጭ ማጎልበት የወጣ

የጨረታ ማሰታወቂያ

ድርጀታችን ሴንድ ኤ ካዉ ኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎችና ዞኖች በርካታ የልማት ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል።

በዚህም መሰረት፦

ድርጅታችን በወላይታ ዞን  ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጉሩሞ ውይዴ ቀበሌ አንድ የንጹህ መጠጥ ውሃ ምንጭ የማጎልበት ሥራ ለማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች ወይም ተጫራቾች መሳተፍ እንደምትችሉ እንገልጻለን።

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና የ2014 ዓ.ም ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ  (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ።
  3. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (TIN NUMBER) ያለቸው።
  4. ተጫራቾች GC ደረጃ 6 ወይንም WWC ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ ያላቸዉ መሆን አለባቸዉ።
  5. የጨረታዉን ማስከበሪያ (CPO) 10,000 (አስር ሺህ ብር) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ከሥራው ጋር ተያያዥነት ያለዉ ከዚህ ቀደም የሰሩበትን ሁለትና ከዚያ በላይ የመልካም ሥራ አፈጻጸም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዋናዉንና ኮፒዉን በሰም በታሸገ እንቭሎፕ ማቅረብ አለባቸዉ።
  8. የጨረታ ማስገቢያው ሃሙስ ሃምሌ 28 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 4፡00 የሚያበቃ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4፡15 የሚከፈት ይሆናል።
  9. የጨረታዉ አሸናፊ ከተገለፀ በኃላ አሸናፊው ተጫራች በ2 (ሁለት) ቀናት ዉስጥ በአካል በመቅረብ ዉል መፈፀም አለበት ይህ ካልሆነ ግን ለጨረታዉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ይሆናል።
  10. ተጫራቾች የመስክ/ሳይት ምልከታ ማድረግና ከቀበሌው ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  11. ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 7 /ሰባት/ የስራ ቀናት ብቻ አየር ላይ የሚቆይ ይሆናል።
  12. ማሳሰቢያ፡_ የጨረታ ሰነዱን ወላይታ ሶዶ ሉትራን/አሜሪካን ኢንተርናሽናል አካዳሚ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በስራ ቀንና ሰአት በመምጣት መውሰድ ይቻላል። የጨረታ ሰንድ ማስገቢያው ስፍራውም በዚሁ ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ይሆናል።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 180 4011/046 180 4463 ወይም በሞባይል ቁጥር 0920 17 40 27/0911 31 93 67 በመደወል መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
Save Tender