ሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት ፕሳስቲክ ሽፋን ሆኖ የተለበዱ ሲናር ላየን ደብተሮችን እንዲሁም የፅህፈት መሳሪያዎችን መግዛት ይፈልጋል
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት ለ2015 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን የድርጅቱ ታቃፊ ስሆኑ ተማሪዎች ፕሳስቲክ ሽፋን ሆነ የተለበዱ ሲናር ላየን ደብተሮችን፡-
- 1ኛ ባለ 50 ቅጠል ባለ መስመር፤
- 2ኛ, ባለ 32 ቅጠል ባለ መስመር
- 3ኛ, ስኩዌር ባለ 50 ቅጠል ደብተሮችን፤
- 4ኛ, ኬኒያ ቢክ እና ቡና እስክሪብቶዎችን፣
- 5ኛ HB እርሳሶችን በየትምህርት ክፍል ደረጃቸው የሚያስፈልጋቸውን መጠን መግዛት ይፈልጋል
በመሆኑም ፡-
- ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ሆነው በዘርፉ የታደሰ የሥራ ፈቃድ ያላቸው እና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር) በሲፒኦ በድርጅታችን ስም ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከድርጅቱ በ200 ብር በመግዛት ከላይ በቅደም ተከተል የተጠቀሱትን 5 አይነት የግዢ ዝርዝሮችን በድርጅታቸው ዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ የእያንዳንዱን እቃ ነጠላ ዋጋ እስከነ ቫቱ በማስቀመጥ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የተጠየቁትን ሰነዶች በማሽግ ቡኢ ከተማ በሚገኘው የሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ህትመት ገጽ ላይ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በሰባት ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ተገኝተው ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።
- ተጫራቾች በተጨማሪም የጨረታውን ሰነድ ሲያቀርቡ ከሚያቀርቡት ከላይ ከተገለጹት ደብተሮች እስኪርብቶዎች እVATና እርሳሶች ለናሙና የድርጅታቸውን ማህተም በማሳረፍ በኤንቨሎፕ አሽገው ቡኢ ከተማ በሚገኘው የሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት ጽ/ቤት የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት የመጨረሻው ሰባተኛ የሥራ ቀን ላይ ከቀኑ 8:00 ላይ ታሽጎ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡኢ ከተማ ሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ ህጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 046-883-0266/0350/0023
(ሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት) ጠይቆ መረዳት ይቻላል።
አድራሻ፦
ሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት፡ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦና ህዝቦች ክልል በጉራጌ ዞን በሶዶ ወረዳ ቡኢ ከተማ ወደ አይመለል በሚወስደው መንገድ ከዋናው አስፓልት መንገድ 100 ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። ቡኢ ከተማ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምህራብ አቅጣጫ ከአለምገና ወደ ቡታጅራ ከተማ በሚወስደው መንገድ ከአዲስ አበባ ከተማ በ103 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።
