ጉድ ኔበርስ ኢትዮጵያ የተለያዩ የምግብ ግብዓቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር GNE 13/2014
ጉድ ኔበርስ ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነ ለትርፍ ያልተቋቋመ አለምአቀፋዊ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን ለድርጅቱ ተጠቃሚዎች የሚሆን የተለያዩ የምግብ ግብዓቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታዉ እንድትሣተፉ ይጋብዛል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
|
1 |
ስንዱ ዱቄት በባለ 25 ኪ.ግ. 2ኛ ደረጃ |
በቁጥር |
8,845 |
|
2 |
ያልተፈጨ ቦቆሎ 50 ኪ.ግ የታሸገ |
በቁጥር |
1,645 |
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸዉ ማረጋገጫ /ክሊራንስ/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛዉም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7(ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ማለትም ከሰኞ አስከ አርብ ከ 2:00 ሰዓት አስከ 10:30 ሰዓት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ልደታ ክ/ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ አህመድ የገበያ ማዕከል 5ኛ ፎቅ በሚገኘዉ ከዋናዉ መ/ቤታችን በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ከፋይናስ ክፍል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከቀረበዉ ጠቅላላ ዋጋ ማለትም በምታቀርቡት በባለ 25 ኪ.ግ ስንዴ ዱቄት ሁለተኛ ደረጃ 2% በባንክ በተመሰከረ ሲፒ.ኦ ብቻ በድርጅቱ ስም በማሰራት ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7ኛዉ ቀን ማለትም ሐምሌ 28 ቀን 2014 ዓ.ም. በጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ባለዉ የዋጋ ማቅረቢያ በግልጽ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረዉ በመሙላት በግርጌው ስም፤ ፊርማና የድርጅታችሁን ማህተም በማኖር ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ በማስገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን።
- ጨረታዉ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7ኛዉ የስራ ቀን ቅዳሜን ሳይጨምር በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ በ4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በድርጅቱ መሰብ/ቢያ አዳራሽ የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዱቄት 5 (አምስት) ኪ.ግ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የትራንስፖ ረት ዋጋን ሲሞሉ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተዘረዘረዉ ማለትም ካሉበት ተቋም አስከ ፕሮጀክት ማቅረቢያ ድረስ የማስጫኛ ዋጋን ጨምሮ መሆን አለበት።
ማሳሰቢያ- ደርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ለበለጠ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር +251-11 557 8614
