የይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ባህርዛፍና የግራቪላ ዛፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር በ2015 በጀት ዓመት በከተማ ክልል በጣም ትላልቅና መካከለኛ የሆኑ በቁጥር 461 (አራት መቶ ስልሳ አንድ ብቻ ) የሆኑ ባህር ዛፍና የግራቪላ ዛፍ በቁሙ በጠቅላላ በመነሻ ዋጋ 461,045 (አራት መቶ ስልሳ አንድ ሺህ አርባ አምስት ብር ብቻ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት
- ተጫራቾች በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /BANK GAURANTEE/ ወይም ክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 50 ሀምሳ ብር ብቻ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ብር በመክፈል ደረሰኙን በመያዝ ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግዥ/ፋይናንስ ክፍል የመጫረቻ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ፣ ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል ማለትም ከላይ የተጠየቁ ዶክመንቶችን በአንድ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ በሁለቱም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 5:30 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግዥ/ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከረፋዱ 5፡30 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:00 ላይ ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
- የጨረታ አሸናፊዎች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ወዲያውኑ ክፍያውን በመክፈል በሶስት ቀናት ውስጥ ዛፎቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል።
- አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/ጽ ቤት
ይርጋዓለም
