Tender Detail

Tender Details

  • Deadline01 Sep 2022, 12:02 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

ፊውቸር ጄኔሬሽን ኦርጋናይዜሽን ለማህበረሰቡ አገልግሎት የሚውሉ 300 ሜትር ኪዩብ ውሀ መያዝ የሚችል (ሲስተርን) የውሀ ማጠራቀሚያ ለማስገንባት ይፈልጋል


የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

ፊውቸር ጄኔሬሽን ኦርጋናይዜሽን ከቻይልድ ፈንድ ባገኘው የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ «በፈንታሌ ወረዳ የተፈጥሮ ጥበቃ እና የምግብ ዋስትና ማረጋገጫ» በተባለው ኘሮጀክት ፋቴሌዲ እና ጡጡጢ ቀበሌዎች ለማህበረሰቡ አገልግሎት የሚውሉ 300 ሜትር ኪዩብ ውሀ መያዝ የሚችል (ሲስተርን) የውሀ ማጠራቀሚያ ብዛት 2 ለማስገንባት ስለሚፈልግ በሙያው ፍቃድ ያላችሁ የግንባታ ባለሙያዎች ወይም ድርጅቶች ቀጥሎ በተመለከተው መስፈርት መሠረት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት መተሐራ ከተማ ከሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 50.00 (ሀምሳ )በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ገዝታችሁ አጠቃላይ የግንባታ ስራ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ድርጅቱ ያሳውቃል።

የጨረታው መስፈርቶች

  1. በሙያው ደረጃ 5 እና ኪዚያ በላይ የግንባታ ፈቃድ ያለው
  2. የዘመኑን ግብር የከፈለና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው
  3. የውሀ ማጠራቀሚያ ሲስተርን እንደዚሁም በተዛማች የግንባታ ስራዎች ካሁን ቀደም መልካም የሥራ አፈፃፀም ያለውና ሰርተፍኬት ወይም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin #) ያላቸው
  5. የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያለው
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 10% (አስር ፐርሰንት ) ማስያዝ (ማቅረብ ) የሚችሉ
  7. ከአሁን በፊት ተዛማች ሥራዎችን በኮንትራት በመውሰድ በአፈፃፀም ችግር የፍርድ ቤት ክስ የሌለበት።

ማሳሰቢያ:-

  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከወጣበት 10 ተከታታይ ቀናት የመጨረሻው የስራ ቀን ጠዋት 4:00 ሰዓት ይሆናል። ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው ሲከፈት መገኘት ይችላሉ።

ፊውቸር ጄኔሬሽንስ ኦርጋናይዜሽን

ስልክ ቁጥር:-0920 35 86 11

0911 89 93 97

ፊውቸር ጄኔሬሽንስ ኦርጋናዜሽን

Save Tender