በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎችን ፣ የፅዳት እቃዎችን ፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎችን እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ፣ የሰራተኞች የደንብ ልብስ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2015 በጀት ዓመት የጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት አገልግሎት የሚውሉ
- የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎችን ፣
- የፅዳት እቃዎችን ፣
- ቋሚ የቢሮ እቃዎችን እንዲሁም
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ፣
- የሰራተኞች የደንብ ልብስ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ አቅራቢዎች የጨረታዉ ሰነድ በአንድ ላይ ተያይዞ ስለሚገኝ በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያላችሁና በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የጨረታዉን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ስለዚህ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቀድ ያላቸው ፣ የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉና በአቅርቦት የተመዘገበበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣ የቫትና ቲኦት (TOT) ተመዝጋቢዎች የሆኑ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 (አምስት ሺህ) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ ፣ የንግድ ድርጅቶች ወይም ግለሰብ ነጋዴ ይህ ጋዜጣ 15/11/2014 ከወጣበት ቀን አንስቶ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ጎሮ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት ድረስ በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 (መቶ) በመክፈል መግዛት ይቻላል። ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 15ኛው የስራ ቀን እስከ 6፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 3 እንዲያስቡ ሆኖ ጨረታው በ6፡00 ላይ ተዘግቶ ለተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቦታ ይከፈታል። አቅራቢዎች የሚቀርቡት እቃዎች ጥራታቸውንና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን አለበት። በሚያቀርቡት የጨረታው ሰነድ ላይ የድርጅቱን ስም አድራሻ ህጋዊ ማህተምና ፊርማ መስፈር አለበት። ለሚወዳዳሩበት ዕቃዎች ከተጫራቾች የሚቀርበው ሰነድ የዕቃውን ዝርዝር ዓይነት ፣ ስምና የተመረተበት ሀገር (brand name) እንዲሁም ዘመን የሚገልፅ ሆኖ የእቃው ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ በደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን የጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት ድረስ ማቅረብ አለበት። ተጫራቾች የዋጋ ማቅረብያውን ሰነድ ኦሪጂናልና ኮፒውን ለይቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርጎ ማቅረብ አለባቸው። አሸናፊው በሚያቀርባቸው ዕቃ ላይ 10 ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ:- መ/ቤቱ የሚገኘው በጂማ መስመር ሆኖ በወሊሶ እና በወልቂጤ መሃል ከአ/አ 134 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ይገኛል።
ስልክ፡- 0113 45 01 17 ወይም 0113 45 06 26
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት
የጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት
