ሳፋሪኮም ቴሌኮሙዩኒኬሽንስ ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ መጋዘን መከራየት ይፈልጋል
መጋዘን ለመከራየት የወጣ ማስታወቂያ
ሳፋሪኮም ቴሌኮሙዩኒኬሽንስ ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ የሚከተሉትን መሥፈርቶች የሚያሟላ መጋዘን መከራየት ይፈልጋል።
- መገኛ ቦታ፡ አዲስ አበባ ውስጥ ከመሐል የከተማ አካባቢ በ20 ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ የሚገኝ ፣ ቃሊቲ አካባቢ ቢሆን ተመራጭ ነው።
- ስፋት፡ 7,000 ካሬ ሜትር ግቢ ሆኖ የሕንፃው ጣሪያ ስፋት 3,000 ካሬ ሜትር የሆነ
- የወለል አጨራረስ፡ የወለል ሥራ ያለቀለትና ለማጽዳት አመቺ የሆነ ፣
- ደኅንነቱ በተጠበቀ ሥፍራ የሚገኝ፡ የራሱ የደኅንነት አጥር ወይም ሌላ የደኅንነት መጠበቂያ የተሟላለት
- በነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ርክክቡ መጠናቀቅ የሚችል
- በዘመናዊ መንገድ የተገነባና ውኃ ፣ ኤሌክትሪክ ፣ መፀዳጃ ቤቶችን ጨምሮ በቂ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ መሠረተ ልማቶች የተሟሉለት
- የፋይበር ኔትወርክ ግንኙነት የተዘረጋለት ወይም ለኦፕቲክ ፋይበር አገልግሎት መስመር በቅርበት የሚገኝ
- ለቢሮ የሚሆኑ ክፍሎች ያሉት
የፍላጎት መግለጫው አላላክ
የመጋዘን ኪራይ አገልግሎት ለመስጠት ፍላጎት ያላቸው አከራዮች ፣ የፍላጎት መግለጫቸውን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ ዓርብ ሐምሌ 22 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ምሽቱ 11 ሰዓት ድረስ በኢ-ሜይል አድራሻ bids@safaricom.et ቀጥሎ የሰፈሩትን በማሟላት መላክ ይኖርባቸዋል።
- የቤቱ ባለቤት ስም (ግለሰብ ወይም ኩባንያ)
- የምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የንግድ ፍቃድና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ኮፒ (ቅጂ)
- የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ኮፒ (ቅጂ) ፣ የባለቤትነት ማረጋገጫ ያቀረቡ ብቻ ማስረጃቸው የሚታይ ይሆናል
- መጋዘኑ የሚከራይበት የሦስት ዓመታት ሙሉ የኪራይ ዋጋ
- ለኪራይ ስለሚቀርበው መጋዘን ከታች የሰፈሩትን ያካተተ የተሟላ መረጃ
- መጋዘኑ የሚገኝበትን ቦታ የሚያሳይ አቅጣጫ ጠቋሚ (ማፕ)
- ቦታውን የሚያሳይ ካርታ
- ሕንፃውን የመጠቀም ፈቃድ
- ጠቅላላ ግንባታው ያረፈበትና ያላረፈበት ቦታ ስፋት
- የንብረቱ ባለቤት መግለጽ የሚፈልጋቸው ተጨማሪ መረጃዎች
ኢ-ሜይሉ በሚላክበት ወቅት ሳብጀክት በሚለው ቦታ ላይ warehouse space for lease" የሚለው መጻፍ አለበት።
- በኢሜይል የሚላኩ ሁሉም ማስረጃዎች ከሃያ ሜጋ ባይት ያነሱ መሆን አለባቸው። ከዚህ በላይ የሆኑ ሰነዶች በጎግል ድራይቭ ሊንክ መላክ ይኖርባቸዋል።
ሳፋሪኮም ዝቅተኛውን ዋጋ ካቀረቡ ባለንብረቶች ጋር ወደ ስምምነት ሊገባ ይችላል።
ማስታወሻ
- ሳፋሪኮም ዝቅተኛውን የዋጋ መሥፈርት ካሟሉ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ብቻ ተጨማሪ ውይይት ያደርጋል።
- ከፍላጎት መግለጫው ዝግጅትና አላላክ ጋር በተያያዘ ያሉ ወጪዎች የፍላጎት መግለጫውን በላከው ግለሰብ (ድርጅት) የሚሸፈኑ ይሆናል።
ማሳሰቢያ
ሳፋሪኮም ቴሌኮሙኒኬሽን ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ጨረታውን ሆነ የተጫራቾችን የፍላጎት መግለጫ ወይም የአገልግሎት መነሻ ሐሳብ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ውድቅ የማድረግና የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው። ድርጅቱ የሚያሳልፈው ውሳኔ የሚጸና ሲሆን ፣ ለተጫራቾች የጨረታውን ውጤት ከማሳወቅ ውጪ በሌሎች ምልልሶች እንዲሳተፍ አይገደድም። ሳፋሪኮም ቴሌኮሙኒኬሽንስ ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ወይም እንደ ሳፋሪኮም ቴሌኮሙኒኬሽንስ ኢትዮጵያ ሆኖ እንዲሠራ ህጋዊ ውክልና የተሰጠው አካል ከዚህ ማስታወቂያ ጋር በተያያዘ የተላኩ ማስረጃዎች ላይ ጥያቄ የማቅረብም ሆነ የማመሳከር መብት አለው።
