በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት የታጠበ ጥሬ ቡና ፣ አልባሳት ፣ ኮስሞቲክስ ፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ኮስሞቲክስ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጹ የተወረሱ ዕቃዎችን በሐራጅና ግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨ.ቁ/01/2015 ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ/ቁ |
ዘርፍ |
የጨረታው ዓይነት |
ዕቃው ያለበት ቦታ |
|
1 |
የታጠበ ጥሬ ቡና |
ግልጽ ጨረታ |
በሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ |
|
2 |
አልባሳት |
ግልጽ ጨረታ |
በሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ |
|
3 |
ኮስሞቲክስ |
ግልጽ ጨረታ |
በሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ እና ሚሌ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ |
|
4 |
ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች |
ግልጽ ጨረታ |
በሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ እና ሚሌ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ |
|
5 |
ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች |
ሐራጅ ጨረታ
|
በሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ |
|
6 |
ኮስሞቲክስ |
ሐራጅ ጨረታ
|
በሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ እና ሚሌ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ |
በመሆኑም ጨረታ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ያለበት ሲሆን በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለበት ሲሆን ለሐራጅ ጨረታ ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ1፡00-5፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመገኘት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሰመራ ጉምሩh ቅ/ጽ/ቤት ውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 15 በመምጣት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና በሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ለኤሌክትሮኒክስ እና ለኮስሞቲክስ ዘርፍ ለእያንዳንዳቸው ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ለጨረታ ዋስትና (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ ስም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION SEMERA BRANCH OFFICE በሚል በባንክ አሰርተው ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የግል ባንክ ከሆነ ከሰመራ እና ከሎጊያ ቅርንጫፎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሆነ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ቅርንጫፎች ከሰመራ እና ከሎጊያ ቅርንጫፎች መዘጋጀት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ
ተ.ቁ
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም
የጨረታው አይነት
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ
የጨረታው መዝጊያ እና የጨረታው መከፈቻ ቀንና ሰአት
1
ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
ግልጽ ጨረታ
እስከ 21/11/2014
22/11/2014 አ.ም ሰአት ተዝግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ሰአት ይከፍታል
2
ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
ግልጽ ጨረታ
እስከ 21/11/2014
22/11/2014 አ.ም 4፡30 ሰአት ይከፍታል
- የጨረታው መክፈቻ ቦታ:- በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ያስያዙትን ዋስትና (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋ
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ጀምሮ በ5 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሜ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን የእቃውን ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል፤ ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።
- ቅ/ጽ/ቤቱ ለጨረታ የቀረበውን እቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስ.ቁ. 033 366 2302 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
