በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የጅማ ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ለውሃ ማከሚያ የሚያገለግል Polyelectrolyte and Calcium hypochlorite በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የጅማ ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ለውሃ ማከሚያ የሚያገለግል ኬሚካል ፡-
- Lot. l. Poly electrolyte and
- Lot.2 .Calcium hypochlorite በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
- ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው።
- ለጨረታው ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት የዕቃ ዋጋ ብር 5% በተረጋገጠ ባንክ (cpo) በድርጅቱ ስም አሰርቶ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፋል በመ/ቤቱ ቀርቦ መግዛት ይችላል።
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የእቃ ስፔሲፊኬሽን ከድርጅቱ በቀረበው መሠረት በግልፅ በመፃፍና ዕቃው ላይም በግልፅ መታየት ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን አሟልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጅማ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቀርቦ ለዚሁ በተዘጋጀ ጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚኖሩት 15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታ የሚያሸንፉት ዕቃዎች የሚያስረክቡበትን ጊዜና ቀን በዋጋ ማቅረቢያ ላይ መግለጽ አለበት። እንዲሁም ኦሸናፊ ድርጅት ማሸነፉን ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በአምስት (5) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል መፈራረም አለበት።
- አሸናፊው ድርጅት ውል ከተፈራረመ በኋላ ዕቃዎቹን በራሱ ወጪ ትራንስፖርት ጅማ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ድረስ ማምጣት አለባቸው።
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
- ከሎት ውስጥ ከተሰጡት ዕቃዎች ዝርዝር በከፊል መወዳደር (Partial Offer) አይቻልም።
- ድርጅቱ ከሰጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ ማስተካከያ ማድረግ እና መሰረዝ (Material Devation) አይቻልም።
- ተጫራቾች በድርጅቱ በዋጋ ማቅረቢያ የድርጅቱ ኦርጅናል ማህተም የጅማ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የሚል ማህተም ባረፈበት ላይ ብቻ የዕቃ ዋጋዎችን ሞልቶ ማቅረብ አለበት። ከድርጅቱ ዋጋ ማቅረቢያ ውጪ የሚመጡ ሰነዶች ዋጋ የላቸውም።
- የጨረታው አሸናፊ የሚለየው(Technical Evaluation +Financial Evaluation +Nontechnical) በተሰጠው ስፔስፊኬሽን መሠረት አሞልቶ በጠቅላላ ድምር አሸናፊ ይሆናል። የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ተከታታይ ቀናት ጠብቆ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። በእለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ድርጅታችን ግዥ እና ፋይናንስ አስ/ስራ ሂደት በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር (047 111 1391) ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
የጅማ ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
ጅማ
