Tender Detail

Tender Details

  • Deadline07 Aug 2022, 10:24 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Equipment And Accessories

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ Tripp Lite Smart UPS Battery በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ Tripp Lite Smart UPS Battery በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ከፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢ ወይንስም ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግስት መ/ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡና የመንግስት ጨረታዎች መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመረጃ መረብ (Website) ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ እና የሚጫረቱበት ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) የሚበልጥ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 40,000 (አርባ ሺህ ብር) በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም CPO ወይም ካሽ ወይም ሌተር ኦፍ ከሬዲት የጨረታው ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  3. በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ሆኖ እለቱ ቅዳሜና እሁድ/ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ድረስ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ። ጨረታውም በ16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ሲሆን እለቱ በዓል/ የእረፍት ቀናት ውስጥ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  5. ይህ ጨረታ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ዘጠና ቀናት ነው።
  6. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

ስልክ ቁጥር፡- (046) 221 26 47/21 21 26

(046) 220 26 47

ፋክስ፡_ (046)220 51 63

221 24 73 

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

የመ.ሳ.ቁ 05

Website፡- WWW.hu.edu.et    

ሀዋሳ

Save Tender