በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ የተለያዩ የአደጋ መከላከያ አልባሳት (Different type of protective Device) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር ኦኩስፋ_3 /አግጨ-39/2014 ዓ.ም.
በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፀውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የተለያዩ የአደጋ መከላከያ አልባሳት (Different type of protective Devise)
1. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር ህጋዊ የታደሰ/አዲስ የንግድ ፈቃድ ፣የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስከር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ/መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚለከተው አድራሻ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00፣ _ ከሰዓት _ ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ ገዝተው በጫረታው መሳተፍ ይችላሉ።
የግዥ ዋና ክፍል
ካሳንችስ ልማት ባንክ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ግብይት ህንጻ ስድስተኛ ፎቅ ኦሞ ኩራዝ -1 እ5 3 ስኳር ፋብሪካዎች ማስተባበሪያ ቢሮ
ስልክ ቁጥሮች፦ 0916 40 55 90/ 0920 71 17 49/0909 19 78 53
አድስ አበባ ካሳንቺስ
ሰርቪስ ዘርፍ ም/ዋና/ ስራ አስኪያጅ
0916041711/0912331733
ኩራዝ
3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ቀጥሎ የተመለከተውን የብር መጠን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሠከረለት (CPO) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
3.1 ለአደጋ መከላከያ አልባሳት የጨረታ ማስከበርያ ብር 50,000 (ሃምሳ መቶ ሺህ ብር) ነው።
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ነሐሴ 6/12/2014 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ነሐሴ 6/12/2014 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
5. የዕቃዎቹ ርክክብ የሚፈፀመው አዲስ አበባ ካሳንቺስ መናኽሪያ ተብሎ በሚጠራው ወይም ጨርጨር ስጋ ቤት ወረድ ብሎ የኦሞ ኩራዝ-3 ስኳር ፋብርካ መጋዘን ይሆናል።
6. ጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው።
7. የጨረታው ማስረከቢያ ዋስትና ፀንቶ የቆያ ጊዜ ለ90 ቀናት ነው።
ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት
