ጣይቱ የትምህርትና የባህል ማዕከል የ2013/14 የበጀት ዘመን ሂሳቡን በበጎ አድራጎት ማህበራት ኤጄንሲ መመሪያ መሰረት ማስመርመር ይፈልጋል
የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ
ጣይቱ የትምህርትና የባሕል ማዕከል በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጄንሲ በመዝገብ ቁጥር 5490 ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነት የተሰጠው ተቋም ነው። ድርጅቱ የ2013/14 የበጀት ዘመን ሂሳቡን በበጎ አድራጎት ማህበራት ኤጄንሲ መመሪያ መሰረት ማስመርመር ይፈልጋል።
ስለዚህም፦
- በሙያው የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው።
- ለበጎ አድራት ማህበራት ኤጄንሲ የሚቀርብ የሂሳብ ምርምራ ሪፖርት የማዘጋጀት ልምድ ያለው ድርጅት። ከላይ የተመለከቱትን ማስረጃዎች በመያዝ ምኒሊክ አደባባይ አጠገብ በቀድሞው አራዳ ወረዳ ፍርድ ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው የማዕከሉ ጽ/ቤት በመገኘትና የስራውን መጠን ከተረዱ በኋላ ስራውን ሰርቶ ለመጨረስ የሚፈጅበትን ግዜና ዋጋ እንዲሁም ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ጨምሮ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ለድርጅቱ ጽ/ቤት ገቢ እንድታደርጉ እናስታውቃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0911 67 29 13
ጣይቱ የትምህርትና የባህል ማዕከል
