ሄጦሳ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን የተወሰነ 5,000 (አምስት ሺህ) ኩንታል ስንዴ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
የስንዴ ጨረታ ማስታወቂያ
ሄጦሳ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን /የተወሰነ 5,000 (አምስት ሺህ) ኩንታል ስንዴ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በሟሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ያስታውቃል።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ከሄጦሳ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒየን ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1(አንድ) መግዛት የምትችሉ መሆኑና ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 8 ተከታታይ የስራ ቀን ብቻ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዚሁ የንግድ ዘርፍ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቹ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታውን 10% በ CPo ወይም በባንክ ጋረንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማቅረብ መጫረት ይችላሉ።
- ጨረታው በ8ኛው የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት 4፡30 በላይ ይከፈታል።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በዩኒየኑ ጽ/ቤት በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0223350888/0223350936 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ላይ በከፊልም ሆነ በሙሉ መሳተፍ ይችላሉ።
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
- የአንድ ኩንታል መነሻ ዋጋ 4,150 (አራት ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ ብር) ነው።
- ተጫራቾች በራሳቸው ትራንስፖርት የገዙትን ስንዴ ያጓጉዛሉ።
- ማሳሰቢያ- ዩኒየኑ ሥንዴውን ኢተያ ካለው መጋዘን ጨረታውን ላሸነፈው አካል ያስረክባል።
- አድራሻችን: - ሔጦሳ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን አርሲዞን ሔጦሳ ወረዳ ኢተያ ከተማ 02 ቀበሌ ከኖክ ማድያ ከፍ ብሎ።
ስልክ ቁጥር 0223350888/0223350936
ሄጦሳ የገበሬዎች ህብረት ስራ
ዩኒየን ኃ/የተወሰነ
