የአርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት (2015 የበጀት ዓመት በዞኑ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ፣ ፈርኒቸር ፣ የጽህፈት መሣሪያዎች ፣ የፅዳት እቃዎች ፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ ፣ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁ-01/2015
የአርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት 2015 የበጀት ዓመት በዞኑ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት
- የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒከስ
- ፈርኒቸር
- የጽህፈት መሣሪያዎች
- የፅዳት እቃዎች
- የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና
- የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፦
- ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ የግብር ከፉይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ እና በፌዴራል፤ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስከር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ለጽህፈት መሣሪያዎች እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይለስ ብር 400.00 (አራት መቶ)፤ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች፤ ለጽዳት እቃዎች፧ እና ደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 350.00 (ሶስት መቶ ሃምሳ) በአርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባን በሂሳብ ቁጥር 1000022696134 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር MWD106 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘኑን ግብር አጠናቀው ለፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16 የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ጨረታው በ16 የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ የስብሳባ አዳራሽ ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ለጽህፈት መሣሪያዎች፤ እና ለመኪና ጎማዎች ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000.00 (አርባ ሺ)፤ ለደንብ ልብስ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ) እንዲሁም፤ ለጽዳት እቃዎች እና ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺ)፤ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንክ በከፍያ ማዘዣ (C.P.O.) ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል።
- አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ከምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ አሰላ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የዞኑ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያስ.ቁፕ 022 238 1142,0911 06 69 44,0912 31 15 26,0912 26 03 21 ይጠይቁ:
አርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት
