Tender Detail

Tender Details

  • Deadline07 Aug 2022, 9:58 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Equipment And Accessories

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ኤሌክትሮኒክስ ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ PQ Master Switching Module ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የስታንዳርድ ፓዎር ካሊብሬሽን ማሽን (Standard Power calibration Machine) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ኤሌክትሮኒክስ ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ PQ Master Switching Module ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የስታንዳርድ ፓዎር ካሊብሬሽን ማሽን (Standard Power calibration Machine) ብዛት 01 (አንድ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶችን የምታሟለ ተጫራቾች እንዲትጫረቱ ተጋብዛችኋል።

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin) ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  3. የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺ ብር) በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ኤሌክትሮኒክስ ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ስም በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለብቻው በፖስታ አሽገው ወይም ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች በሰነዶቻቸዉ ላይ ስማቸዉንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል በሙላትና በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለዉ ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት።
  7. ተጫራቾች የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከኤሌክትሮኒክስ ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ቀናት ዉስጥ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል መዉሰድ ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናዉን እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በታሽı ኤንቨሎፕ ለጨረታው በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸው።
  9. ተጫራቾች የቴክኒካልና የፋይናንሻል ሰነዱን ለየብቻ ለይተዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. ጨረታዉ ይህ ማስታወቂይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን 4፡30 ይዘጋል፤ በዚሁ ዕለትም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንዱስትሪያችን ውስጥ በሚገኘው በሆም ቤዝ ፋብሪካ ይከፈታል።
  11. የጨረታዉ መዝጊያና መከፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
  12. ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚፀናበት ጊዜ ለ60 (ስልሳ) ቀናት ነው።
  13. ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  • አድራሻ- በለገጣፎ 44 ማዞሪያ 4 ኪ.ሜ ገባ ብሎ ለገዳዲ ዉኃ ግድብ አጠገብ ነው።
  • ለበለጥ መረጃ በስልክ ቁጥራችን፦ 0929 04 20 70/0910 27 43 08 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ

ኤሌክትሮኒክስ ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ

Save Tender