በደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ላሉ መኪኖች ለ2015 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ለዚህም ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ለማቅረብ በዘርፉ የተሰማራችሁ አቅራቢዎች፡-
- በዘመኑ የታደሰ ተዛማጅ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ንግድ ምዝገባ ማቅረብ የሚችል።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው።
- የግዥ መጠን ከ200,000 (ከሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይ ሰርትፊኬት ማቅረብ የሚችል።
- የሚገዛውን እቃ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች እያንዳንዱን ሰነድ የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከወረኢሉ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት መውሰድ ይቻላል።
- በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እንዲሁም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ ደረሰኝ በመቁረጥ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ ያልተሞላበት ክፍት ቦታ ካለ ከጨረታ ውድቅ ይሆናል።እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ የበዛበት ከሆነና ፓራፍ ካላደረጉ ከጨረታው ውድቅ ይሆናሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ቀን በአካል የማይገኙ ከሆነ በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላለፈው ውሳኔ የሚከፈትበትን ሰዓት የማያስተጓጉል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸውን በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት ዋና እና ኮፒውን በማያያዝ ሁሉም ሰነዶች ላይ የድርጅቱን ኦርጂናል ማህተም በመጠቀም በጥንቃቄ በ2 ፖስታ በማሸግ በወረዳው ግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ። እንዲሁም ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተዘረዘሩትን ኦርጂናል ሰነዶችን በእጅ በመያዝ ለማመሳከሪያነት በዕለቱ ይዘው መገኘት አለባቸው።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ቀን በ4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በይፋ ይከፈታል። ነገር ግን የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይንም በህዝብ በዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከሚሸጠው የጨረታ መመሪያ ማየት ይችላሉ።
እንዲሁም 033 116 01 99 መደወል ይችላሉ።
በአብክመ የደቡብ ወሎ መስ/ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ዋና ጽ/ቤት
