Tender Detail

Tender Details

  • Deadline28 Jun 2022, 9:50 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ቲፕ ቶፕ (tip top) ፣ የመኪና ባትሪ ፣ ኤሌክትሮድ እና ቤሪንግ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር MSF/LP/07/2022

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፀውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ጥቅል አንድ፡- ቲፕ ቶፕ (tip top) ለሁለተኛ ጊዜ ፣
  • ጥቅል ሁለት- የመኪና ባትሪ (Battery) ለሁለተኛ ጊዜ፣
  • ጥቅል ሶስት- ኤሌክትሮድ (Electrod) ለሁለተኛ ጊዜ፣
  • ጥቅል አራት- ቤሪንግ (Bearing) ለሁለተኛ ጊዜ፣ በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
  1. ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን የአገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሠዓት ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ህንፃ ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220 የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሠነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ የአቅራቢዎች የምዝገባ ሠርተፍኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቢያንስ 2% በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ (Proforma invoice) ላይ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እ.ኢት.አ. ሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ከጠዋቱ 4:00 ሠዓት ድረስ ሜክሲኮ ፊሊፕስ ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 119 ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው በዕለቱ ሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 119 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  6. ፋብሪካው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 011 550 5607, 011 550 5821

ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ሕንፃ

አዲስ አበባ

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ

Save Tender